ኦሮሚያ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሸን የህግ ታራሚዎች ለምግብ አቅርቦት የሚውል ጥሬ እህል ማጣፈጫ እና የማገዶ እንጨት ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ለአንደኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የምሥራቅ ባሌ ዞን ማረሚያ ቤት አስተዳደር ፅ/ቤት ውስጥ ለሚገኙት የህግ ታራሚዎች በምግብ አቅርቦት የሚውል ጥሬ እህል ማጣፈጫ እና የማገዶ እንጨት ለ2019 ዓ.ም በጀት ለአንደኛ ዙር ከሀምሌ 1/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 30/04/2019 ዓ/ም ለ6 (ስድስት) ወር በሚቆይ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በዚህ መሰረት ማንኛውም በጨረታ ውሉ መካፈል የሚፈልግ ድርጅት ወይም ግለሰብ፡

  1. የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ወይም ቢሮ የዘመኑን የስራ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና አግባብነት ያለው 2018 የታደሰ ንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸው መሆን ይጠበቅባቸዋል።
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(TIN)የተመዘገቡ ወይም የተጨማሪ እሴት ታክስ(VAT) ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው።
  3. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 30(ሰላሳ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከዞኑ ማረሚያ ቤት አስተዳደር ፅ/ቤት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዶቻቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በዞን ማረሚያ ቤት አስ/ፅ/ቤት ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር አለባቸው።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከመቶ ሁለት (2%) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (CPO) እና የምግብ እህል ናሙና ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው።
  6. በጥቃቅን እና አነስተኛ ንግድ ተደራጅቶ የበሰለ ምግብ ለማቅረብ የሚቀርቡ ማህበራት ቅድሚያ ይሰጣቸዋል። ይህ ካልተገኘ በጥሬ እህል እናወዳድራለን።
  7. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀን በአየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን በስራ ቀን ከረፋዱ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ያስገቡበት ሳጥን ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት በዞኑ ማረሚያ ቤት አስ/ፅ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም የህግ ታራሚ ኮሚቴዎች እና የማረሚያ ቤቱ ጨረታ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት ይከፈታል።
  8. የዞኑ ማረሚያ ቤት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  9. በማረሚያ ቤቱ ውስጥ በተዘጋጀ ማብሰያ ቤት ውስጥ ምግብ አብስሎ ማቅረብ የሚችል

ማረሚያ ቤቱ የሚገኙበት ከተማ

ተ.ቁ

የዞን ማረሚያ ቤት

የሚገኙበት ከተማ

1

የምሥራቅ ባሌ ዞን ማረሚያ ቤት

ጊንር

 ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09 11 64 52 76 / 09 11 80 38 91 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።

በኦሮሚያ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሸን

ጊኒር

የምሥራቅ ባሌ ዞን ማረሚያ ቤት አስተዳደር/ፅ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-25
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀን በአየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን በስራ ቀን ከረፋዱ በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-25 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀን በአየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን በስራ ቀን ከረፋዱ በ4፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Bale Zone Correctional Facility
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 30.00 ብር
  • Published: Jun 10, 2026
  • Posted at: 2026-06-10T08:38:00.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders