በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የጊዶሌ ማረሚያ ተቋም የምግብ እህል፣ የምግብ ማጣፈጫ እና ማገዶ እንጨት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የጊዶሌ ማረሚያ ተቋም በ2019 በጀት ዓመት በተቋሙ ሥር ለሚገኙ የሕግ ታራሚዎች የምግብ እህል ፣የምግብ ማጣፈጫ እና ማገዶ እንጨት ከሐምሌ 01/2018 እስከ ሰኔ 30/2019 ዓ.ም ድረስ ከዚህ በታች ያለ መስፈርቶችን ከሚያሟሉ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር/TIN-NO/ ያላቸው
- ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ
- የጨረታ ማስከበሪያ ለምግብ እህል ብር 30,000/ ሰላሳ ሽህ ብር/ ለሌሎች ለእያንዳንዳቸው ብር 5,000/አምስት ሽህ ብር/ በመረጡት ዘዴ ማለትም በባንክ በተመሰከረ CPO በጥሬ ገንዘብ ወይም የባንክ ዋሰትና ማቅረብ ይችላሉ የጨረታ ሰነዱን ጊዶሌ ማረሚያ ተቋም ቢሮ ቁጥር 2 ድረስ በመቅረብ የማይመለስ 100/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- የገዙትንም ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በማዘጋጀት በሁለት በተለያዬ ፖስታ በማሽግ ኦርጅናሉ ላይ ኦርጅናል ኮፒው ላይ ኮፒ ብሎ በመጻፍ ፊርማና ማህተም በማድረግ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ተቋሙ ባዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውሰጥ ማስገባት ይችላሉ።
- የጨረታ ሣጥኑ በ16ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል።
- 16 ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ወደ ቀጣዩ የሥራ ቀን ይተላለፋል።
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታ ሂደቱን አያስተጓጉልም፡፡ የጨረታው አሸናፊ ተለይቶ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ካሉት 7 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋለ አሸናፊው የጠቅላላ ዋጋውን 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መግባትና በገባው ውል መሠረት ዕቃዎችን እስከ ተቋሙ ንብረት ክፍል ድረስ የማድረስ ግዴታ አለበት።
- ተቋሙ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 046 774 0595/360/021/359 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የጊዶሌ ማረሚያ ተቋም
Tender details
- Deadline: 2026-06-25
- Publishing entity: Gidole Correctional Facility
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published: Jun 10, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.