የሀዋሳ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም የምግብ እህል ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም ለህግ ታራሚዎች ምግብ አገልግሎት የሚውል የምግብ እህል ለመግዛት በዘርፉ ከተሠማሩ ነጋዴዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ነጋዴዎች መወዳደር ይችላሉ፡-
1. በዚህ ዘርፍ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑ ግብር የከፈሉ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸውና ለአቅራቢነት የተመዘገቡ የንግድ ምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
2. በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ የሚገለፀውን እህል አይነት ለ12 ወራት የሚፈለገው መጠን ጥራትንና ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በየወሩ እስከ ተቋሙ ቅጥር ግቢ ድረስ አምጥተው ማስረከብ ይኖርባቸዋል።
3. ማንኛውም ተጫራች በተራ ቁጥር 1 የተገለፁትን ህጋዊ ማስረጃዎች ለጨረታው ከሚቀርበው ዋጋ ጋር ዋናውንና ኮፒውን አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበርያ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ በባንክ በተረጋገጠ CPO 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር ከዋናው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. የጨረታው ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኢንቨሎኘ በሰነድ ላይ በተገለፀው አድራሻ በተከታታይ 15 ቀናት ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. የጨረታው ሳጥን የሚታሸገው በአስራ አምስተኛ ቀን በ 4፡00 ሰዓት ሲሆን የጨረታ ሳጥን የሚከፈተው በዕለቱ ከጧቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ይከፈታል ይህ ቀን የበዓልም፣ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል።
7. ማንኛውም ተጫራች የእህል ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ አንድ ቀን ቀደም አድርጎ በማስገባት ጥራቱን ለጨረታ ኮሚቴ ማሳዬት አለበት
8. ተጫራቾች ከሀዋሳ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም ግ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/ሥ/ሃደት ቀርበው ዝርዝር ሰነዱን 200 (ሁለት መቶ) ብር በማይመለስ በመክፈል መግዛት ይኖርባቸዋል።
ማሳሰብያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ መረጃ - በስልክ ቁጥር ፡-046-212-8747 መደወል ይችላሉ።
የሲዳማ ብሔራዊ ክልል መንግስት ሀዋሳ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም
Tender details
- Deadline: 2026-06-25
- Publishing entity: Hawassa Central Prison Institute
- Bid bond: 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር)
- Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
- Published: Jun 11, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.