አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዋናው ግቢ ፎረም ህንጻ ያሉ ቦታዎችን ለተለያዩ አገልግሎቶች (ለመጻህፍት ቤት፤ ለእስቴሽነሪና ለቢሮ አገልግሎት) ቤቶችን በግልጽ ጨረታ ለማከራየት ይፈልጋል
Description
የንግድ ቤቶች ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር፡-አአዩ/ብግጨ/የሱቅ/ኪራይ/007/2018/26
1. የተጫራች ስም-
2. የተጫራች አድራሻ አዲስ አበባ...... ክ/ከተማ........................
ወረዳ...........................የቤት ቁጥር ........................ ስልክ ቁጥር.............
3. የንግድ ፈቃድ ቁጥር ..............
4. ቲን ሰርተፍኬት ቁጥር.....................
5. የስራው አይነት
6. የሚጫረቱበት ክፍል ቁጥር......
7. ተጫራቾች የሚጫረቱበት የአንድ ካሬ ሜትር ዋጋ ቫትን ጨምሮ.........
ማሳሰቢያ፡-
1. አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዋናው ግቢ ፎረም ህንጻ ያሉ ቦታዎችን ለተለያዩ አገልግሎቶች (ለመጻህፍት ቤት፤ ለእስቴሽነሪና ለቢሮ አገልግሎት) ቤቶችን በግልጽ ጨረታ ለማከራየት ይፈልጋል።
2. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ከታች በተገለፀው አድራሻ እስከ ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም. እስከ 8፡00 ሰአት ድረስ ጨረታውን ለያዘው ሰው ማስረከብ ወይም ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ። ዘግይተው የቀረቡ የጨረታ መልሶች ተቀባይነት የላቸውም። በጨረታው ላይ ለመገኘት በፈለጉ ተጫራቾች ወይም የተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም በ8፡30 ሰአት ይከፈታል።
3. ከዚህ የጨረታ ሰነድ ጋር የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና ቲን ሰርተፍኬት መያያዝ አለበት።
4. የጨረታ አሸናፊዎች የኪራይ ውል መዋዋል የሚችሉት ለጨረታ ባስገቡት የንግድ ፈቃድ ስም ብቻ ነው።
5. በጨረታ ያሸነፉበትን ክፍል በምንም ዓይነት ለሌላ ወገን ስም ማዞርም ሆነ ተከራይቶ ማከራየት የማይቻል ሲሆን ይህንን ለማድረግ የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጪ እንደሚሆኑ እና የኪራይ ውሉ እንደሚሰረዝ ለማሳሰብ እንወዳለን።
6. ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000087392067 ገቢ በማድረግ የባንክ ደረሰኝ ይዘው በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
8. ይህ የጨረታ መጋበዣ ሰነድ የሚያካትታቸው ዋና የሚከራዩ ቦታዎች ዝርዝር እና የሚከራይ ቦታውን የሚያሳይ ዲዛይን ይሆናል።
9. ይህ የኪራይ አገልግሎት ጨረታ ታሳቢ የሚያደርገው በአገር ውስጥ ለሚፈፀም የአገልግሎት ሽያጭ (የምክር አገልግሎት አይጨምርም) የሚውል መደበኛ የጨረታ ሰነድ ይሆናል።
10. ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የጨረታ ሰነዱ የሚሸጥበት አድራሻ
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 6ኪሎ ዋናው ግቢ የአስተዳደር ህንፃ ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 307
ቁጥር +251 11 124 3290
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
Tender details
- Deadline: 2026-06-22
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-06-22 14:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Ababa University
- Buyer TIN: 0000970957
- Buyer address: Foreign Purchasing DivisionYekatit 12, Martyr's SquareAddis AbabaEthiopia
- Bid bond: 20,000.00 ብር
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: Jun 11, 2026
- Posted at: 2026-06-11T08:29:59.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.