የደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር መሬት መምሪያ ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች ማለትም ለመኖሪያ እና ለንግድ አገልግሎት የሚውሉ ቦታዎችን በግልፅ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል
Description
የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
1. የጨረታ ዙር 25ኛ
2. የጨረታው አይነት መደበኛ
3. የደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር መሬት መምሪያ ጫጫን ጨምሮ በሁሉም ክ/ከተሞች የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 እና ይህንኑ አዋጅ ለማስፈፀም የአብክመ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ ባወጣው ደንብ ቁጥር 103/2004 በክፍል 3 በአንቀፅ 10 በንዑስ አንቀፅ 1 በፊደል ተራ ከ"ሀ" እስከ "ሠ" በተዘረዘረው መሰረት ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች ማለትም /ለመኖሪያ ለንግድ አገልግሎት የሚውሉ ቦታዎችን በግልፅ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መጫረት የሚፈልግ ሰው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 1000/ አንድ ሺህ ብር በመከፈል የደ ብርሃን ከተማ አስተዳደር መሬት መምሪያ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 10 ዘወትር በስራ ሰአት መግዛት የሚቻል መሆኑን እናሳውቃለን።
4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው መሰረት መሆን ይኖርበታል።
5. ተጫራቾች ሁለት የተለያዩ ተመሳሳይ ፖስታዎችን በማዘጋጀት 1ኛ ክፍል ሁለት የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን እና ክፍል ሶስት የጨረታ ሀሳብ ማቅረቢያ ሰነዱን 2ኛ ሲፒኦን ሁለቱን ሰነዶች አንዳንድ ኮፒ በማድረግ ኦርጅናሉን ለብቻ ኮፒውን ለብቻ በተለያዩ ፖስታዎች በማሸግና በፖስታዎቹ ላይ ኦርጅናል ወይም ኮፒ በማለት ለይቶ በመፃፍ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ፖስታውን እስከ 10ኛው(አስረኛው) ቀን 11፡00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 7 ኦርጅናሉን ሰነድ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ኮፒውን ሰነድ ደግሞ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
6. ጨረታው የሚዘጋው ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ በ10ኛው ተከታታይ የስራ ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰአት ላይ ይሆናል።
7. ቦታውን መጐብኘት ለሚፈልግ ተጫራች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገለፀው መርሐ ግብር መሰረት የምናስጐበኝ ይሆናል።
8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር መሬት መምሪያ ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው አዳራሽ፡፡ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ጨረታው ይከፈታል።
9. የጨረታ መከፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበአል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰእት ላይ ይከፈታል።
10.ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በጨረታ ሰነዱ ላይ እና በመምሪያው ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ እንዲሁም በዌብ ሳይት WWW.mudc.Gov.et ማግኘት ይችላሉ።
11.ከመሥሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር መሬት መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-06-23
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ፖስታውን እስከ 10ኛው(አስረኛው) ቀን 11፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-06-24 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት
- Region: Amhara
- Publishing entity: የደብረ ብርሃን ከተማ መሬት አስተዳደር ቢሮ ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት
- Bid document price: 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/
- Published: Jun 12, 2026
- Posted at: 2026-06-12T07:08:55.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.