የአሶሳ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ የተለያየ እህል፣ የወጥ እህል እና የፅዳት እቃ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በቤ/ጉ/ክ/መ/የአሶሳ ዞን ማ/ቤቶች በ2019 የበጀት ዓመት ለህግ ታራሚዎች አገልግሎት የሚውል የተለያየ እህል ፣የወጥ እህል እና የፅዳት እቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ ለተጫራቾች የተዘጋጀ መደበኛ የጨረታ ሰነድ ነው።
የአሶሳ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ በስሩ ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች ከሀምሌ 01/11/2018 እስከ ታህሳስ 30/04/2019 ዓ/ም ድረስ ያለውን ቀለብና የተለያዩ የወጥ እህሎች እና የንፅህና እቃዎችን ከዚህ በታች በዝርዝር የተመለከተውን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ሠርገኛ ጤፍ፣ ነጭ ማሽላ፣ ከአተር የተፈጨ ሽሮ፣ ሻይ ቅጠል፣ ኤግል ካሜራ(እርሾ)፣ ከኖር የወጥ ማጣፈጫ፣ ቀይ ሽንኩርት፣ በርበሬ፣ ፓስታ፣ አጃክስ፣ ጨው፣ ባቄላ ክክ፣ሩዝ የሚቀቀል፣ ድንች፣ የዳቦ ዱቄት፣ ኑግ፣ ስኳር፣ የምግብ ዘይት፣ ማጂ ማክስ(Magi Max)ዳቦ ማሻሻያ፣ ምስር ክክ፣ አተር ክክ፣ ማካሮኒ እና የልብስ ሳሙና በጨረታ አወዳደሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በጨረታ መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች :-
1. በተሰማሩበት የስራ መስክ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡-
2. የገንዘብ ሚኒስቴር/ የክልሉ ገ/ኢ/ል/ቢሮ የአገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት / ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡-
3. ተጫራቾች እያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ እና የውል ስምምነት ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/በመከፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት አሶሳ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ ግ/ፋ/ንብ/ አስ/ቢሮ ቀርቦ መግዛት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ /ማስያዥ/10,000/ አስር ሺህ ብር በባንክ በተመሰከረለት ሲፒአ ወይም በጥሬ ማስያዝ አለባቸው።
5. ተጫራቾች የሚሸጡበትን ዋጋ በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ /ፖስታ/ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በተቋሙ በመገኘት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
6. ተጫራቾች በሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን በሙሉ ወይም በከፊል በመሙላት መወዳደር ይችላሉ።
7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከወቅቱ የገበያ ዋጋ ጋር የተጣጣመ መሆን አለበት።
8. አሸናፊ ድርጅቶች ለውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው
9. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 7፡30 ሰዓት ታሽጎ ወዲያውኑ በ8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታ መክፈቻ ዕለት ባይገኙም የጨረታ አከፋፈት ሂደቱ አይስተጓጎልም ፡፡ ሆኖም ግን የጨረታ መክፈቻ ቀናት በበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
10. ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ጨረታው በሚከፈትበት አብሮ መቅረብ አለበት።
11. ቫት ተመዝጋቢ ወይንም ቲኦቲ ደረሰኝ ያሳተሙ መሆን አለባቸው።
12. ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ -- 09-17-85-62-51/09-12-79-31-46
ማሳሰቢያ፡- ዋጋ ማቅረብ የምትችሉት በገዛችሁት ሰነድ ብቻ ይሆናል።
ሰነዱ አስፈላጊው መረጃ ተሞልቶና የድርጅቱ ማሕተም ተመትቶ ከዋጋ ዝርዝር ጋር የሚመለስ ይሆናል፤
በቤኒሻጉል/ጉ/ክ/መ/የአሶሳ ዞን ማ/ቤቶች መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-06-27
- Bid closing time: 13:30
- Bid closing (note): ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 7፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-06-27 14:00
- Bid opening (note): ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት
- Region: Beneshangul Gumuz
- Publishing entity: Asossa Zone Correctional Facility
- Bid bond: 10,000.00 ብር
- Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Published: Jun 12, 2026
- Posted at: 2026-06-12T07:22:19.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.