የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመበት አየሉ ደምሴ እና የፍ/ባለዕዳ ሀይሉ ጎንፋ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/121731 በ12/03/218ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ እና በኮ/መ/ቁ/123822 በ8/4/2018ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 04 በይዞታ መለያ ቁጥር AA000070407526 የሆነ በአየለ ደምሴ ሄይ እና ኃይሉ ጎንፋ ጉርሙ ስም የተመዘገበ በሰሜን ዲባባ ጉርሜሳ በደቡብ መንገድ በምስራቅ ቄስ ፍስሀ ከበደ እና በምዕራብ ቢላል ያሲን የሚገኙ አጎራባቾች ሲሆኑ የቦታ ስፋት 219ካ/ሜ የቤቱ ስፋት 96.58 ካ/ሜ ለይዞታው ተደራሽ የሚሆን የ25 ካ.ሜ ስፋት ያለው መንገድ ለይዞታው ተደራሽ ሲሆን የተጠቀሰው መንገድ የተያዘውን 7.25 ካ.ሜ ይነከዋል በተጠቀሰው መንገድ የሚከናወን አዲስ ግንባት በተመለከተ ከተጠቀሰው መንገድ አቅጣጫ በኩል 3 ሜትር ሴት ባክ መጠበቅ አለበት እንዲሁም ከሌላ ባክ ቀሪ 500 ካ.ሜ እና 20 ሜትር የይዞታ የፊት ገጽ መሆን ይኖርበታል፡፡ የሆነ ቤት የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 7,377,906 (ሰባት ሚሊዮን ሶስት መቶ ሰባ ሰባት ሺህ ዘጠኝ መቶ ስድስት) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን። ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-15
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-07-15 10:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
  • Bid bond: 25%
  • Published: Jun 12, 2026
  • Posted at: 2026-06-12T07:28:49.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders