የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ የትራንስፖርት አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን ማግኘት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፣-ኢኤስክ/ግጨ-05/2018
ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ ለ2019 በጀት ዓመት የሚሆን የትራንስፖርት አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን ማግኘት ይፈልጋል።
|
ተቁ |
የዕቃው ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት |
የጨረታ መክፈቻ ቀንናሰዓት |
|
1 |
የትራንስፖርት አገልግሎት |
30,000 |
15/10/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት |
15/10/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት |
ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ድርጅት ወይም ግለሰብ ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
1. የትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢ ዘርፍ የተሰማሩበት የዘመኑ ግብር የተከፈለበት የንግድ ፈቃድ ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የታደሰ የታከስ ክሊራንስ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል የግብር መለያ ቁጥር ያለው በጨረታ መሳተፍ ይችላል።
2. ተጫራቾች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት፣ ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ በመደበኛ የስራ ሰዓት የስፖርት ክለቡ ጽ/ቤት በመገኘት መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Security) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን እና የጨረታ ማስከበሪያቸውን ስማቸውን እና ጨረታ ቁጥሩን በመግለፅ ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ድረስ ብቻ በተጠቀሰው አድራሻ ብሔራዊ ቲያትር አካባቢ ናይል ኢንሹራንስ 10ኛ ፎቅ በሚገኘው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ ጽ/ቤት ማስገባት አለባቸው።
5. ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት ብሔራዊ ቲያትር አካባቢ ናይል ኢንሹራንስ 10ኛ ፎቅ በሚገኘው ስፖርት ክለቡ ጽ/ቤት ይከፈታል።
6. ስፖርት ክለብ ለሚፈጽመው ለስፖርተኞች አገልግሎት የሚሆን የትራንስፖርት አገልግሎት የፋይናንስ ሰነዳቸውን በተለያየ ኤንቨሎፕ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው። በተጨማሪ ለሚወዳደሩበት ማቅረብ ይገባቸዋል።
7. ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ-ሥርዓት መሆንኑ አስመልክቶ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ መመሪያ መሠረት ሲሆን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የሚገልፅ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የግብር ከፋይ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርበታል።
8. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
9. በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፤
10. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር፡- 011-1-55-34-49-49 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ
Tender details
- Deadline: 2026-06-22
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-06-22 14:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: የኢትዮ-ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ
- Bid bond: 30,000 ብር
- Published: Jun 12, 2026
- Posted at: 2026-06-12T08:27:50.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.