የምስራቅ ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤት በስሩ ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች የበሰለ ምግብ አቅርቦት ከሐምሌ 1 ቀን 2018 እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2019 ለ6 (ስድስት) ተከታታይ ወራቶች የሚቆይ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎት ለማግኘት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የተጫራቾች መመሪያ
የምስራቅ ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤት በወባ በጀት ዓመት በስሩ ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች የበሰለ ምግብ አቅርቦት ከሐምሌ 1 ቀን 2018 እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2019 ለ6 (ስድስት) ተከታታይ ወራቶች የሚቆይ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎት ለማግኘት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተገለፀውን መስፈርት የሚያሟሉ ድርጅቶች እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል።
1. ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና ለዚሁ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ እና የንግድ መለያ ቁጥር (TIN Number) ያላቸው እዲሁም አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ ስራ ልምድ ያላቸው ሆኖ ለዚሁ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች በፌዴራል ገንዘብ ቢሮ የአቅራቢዎች መዝገብ ዌብሳይት ላይ ተመዝግበው ያሉ እና በአሁኑ ወቅት ዌብሳይቱ ላይ መገኘታቸውን የሚያመላክት ኮፒ ማስያዝ የሚችሉ ወይም በከልሎች ገንዘብ ቢሮ የአቅራቢዎች መዝገብ ላይ የተመዘገቡ ሆኖ ለዚሁ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የምግብ ማቅረቢያ ሜኑ ሙሉ በሙሉ መረዳት ይኖርባቸዋል።
5. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለፀውን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይችልም።
6. የሚቀርቡ የበሰለ የምግብ አይነቶች በተሰጠው እስፔስፊኬሽን መሰረት አሟልቶ ካልቀረበና ማንኛውም ስህተት ቢፈፀም ኃላፊነቱ የተጫራቹ የአቅራቢው ድርጅት ይሆናል። እንዲሁም የታራሚዎቹ ምግብ የሚዘጋጀው በማረሚያ ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው ኩሽና ውስጥ ሆኖ የምግብ የተለያዩ ማጣፈጫዎች እና የማገዶ ዕንጨት እንዲሁም ምግብ ማብሰያ እቃዎች፣ ማንኛውንም ለምግብ ማብሰያ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች ሙሉ በራሳቸው ትራንስፖርት ወጪ ማረሚያ ቤቱ ድረስ ማቅረብ እንደሚኖርባቸው ማወቅ ይኖረባቸዋል። ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 563,154.00 (አምስት መቶ ስልሳ ሶስት ሺህ አንድ መቶ ሃምሳ አራት ብር ብቻ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። በጨረታው የተሸነፉትም ተሸናፊነታቸው እንደተረጋገጠ ለጨረታ ማስከበሪያ በዋስትና ያስያዙት CPO ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
7. አሸናፊው ድርጅት ከማረሚያ ቤቱ ጋር ውል መፈራረም ይኖርበታል። ተጨማሪ ማረሚያ ቤቱ የሚሰጠውን ደንብ እና መመሪያ አክብሮ ለመስራት ግዴታ መሆኑን ማወቅ ይኖርበታል።
8. አሸናፊው ድርጅት በውሉ መሰረት የበሰሉ ምግቦችን በቀን ለአንድ የህግ ታራሚ በተቀመጠው ሜኑ መሰረት ሳያቀርብ ቢቀር ውል ሰጪው በመንግስት የግዥ መመሪያ ቁጥር 02/2004 እና FA 1/2009 እንዲሁም አዋጅ ቁጥር 157/2002 መሠረት ህጋዊ እርምጃ መውሰድ የሚችል መሆኑን መረዳት ይኖርበታል።
9. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የበሰሉ ምግቦች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ ብር) በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት (15) ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን በምስራቅ ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤት ፋይናንስና አስተዳደር በመቅርብ መግዛት ይችላሉ።
10.ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና 2 /ሁለት/ ኮፒውን በተናጠል በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ አሽገው ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን የድርጅቱን ማህተምም ማድረግ ይኖርባቸዋል።
11 የጨረታ ሰነዱ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት (15) የስራ ቀናት ከ2፡30 እስከ 11፡30 ይሸጥና ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ መሸጥ ከጀመሩበት ቀን ጀምሮ እስከ (16) አስራ ስድስተኛው የስራ ቀን እስከ 4 ሰዓት ድረስ ለጨረታው ሰነድ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገብቶ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ማለትም በአስራ ስድስተኛው (16) የስራ ቀን ከቀኑ 5፡00 ተጫራቾች ወይም በጨረታው ለመካፈል የፈለጉ ማናቸውም ወኪሎቻቸው እንዲሁም የህግ ታራሚ ኮሚቴዎች እና ኮሚቴዎች በተገኙበት ይከፈታል። ይህ አስራ ስድስተኛው 16 የስራ ቀን አመት በዓል በካላንደር ዝግ ከሆነ በቀጣዩ ቀን ይሆ'ናል።
12. ማንኛውም ተጫራች ከሚወዳደሩባቸው የምግብ አህል ውስጥ አንድ አንድ ኪሎ ግራም ደረጃውን የጠበቀ ጤፍ፣ የምስር ክክ፣ የአተር ክክ፣ የተፈጨ በርበሬ፣ የዳቦ ዱቄት ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
13. ማንኛውም ተጫራች ማረሚያ ቤቱ በሚገኝበት አዳማ ከተማ ውስጥ የእህል ማከማቻ መጋዘን (እስቶር ) ያላቸው ሆኖ ለዚሁም ማስረጃ ማቅረብ ይኖረባቸዋል።
14 ማንኛውም ተጫራች የመወዳደሪያ ዋጋ ለቁርስ፣ ለምሳ እና ለእራት ለአንድ የህግ ታራሚ ብር 40.60 (አርባ ብር ከ60/100) በመወዳደር የበሰለ ምግብ ማቅራብ የሚችል መሆን አለበት። ለዚሁም የማቅረብ አቅሙን የሚያረጋግጥ ከፍተኛ የገንዘብ መጠን የያዘ የባንክ እስቴትመንት መረጃ ማቅረብ ይኖርበታል።
15. አሸናፊው ድርጅት ጨረታውን ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀን ውስጥ ቀርቦ የውል ማስከበሪያ 10% ብር 2,815,772.00 (ሁለት ሚሊዮን ስምንት መቶ አስራ አምስት ሺህ ሰባት መቶ ሰባ ሁለት ብር ብቻ የውል ማስከበሪያ CPO ማቅረብ ይኖርበታል።
16. ከዚህ በላይ በተገለጸው መሰረት ተጫራቾች የጨረታ ግዴታ ባይወጡ ወይም ውሉን በአግባቡ ሳይፈጽሙ ቢቀሩ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘውን ገንዘብ ለማረሚያ ቤት ገቢ ሆኖ በግዥ መመሪያ ቁጥር 02/2004 እና FA 1/2009 እንዲሁም በአዋጅ ቁጥር 157/2002 መሠረት ማረሚያ ቤቱ ህጋዊ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን ማወቅ ይኖርበታል።
17. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ ማብራሪያ፤“ማስተካከያ ሃሳብ እና ጥያቄ ካለው ጨረታው ከመከፈቱ ከ5 ቀን በፊት ማረሚያ ቤቱ ማቅረብ ያለበት መሆኑን ማወቅ ይኖርበታል። እንዲሁም ማረሚያ ቤቱ በጨረታ ሰነዱ ላይ የማስተካከያ ወይም ማሻሻያ ሃሳብ ካለው ጨረታ ከመከፈቱ 5 ቀን በፊት ለተጫራቾች ማሳወቅ የሚችል መሆኑን መረዳት ይኖርባቸዋል። ይህ ሳይሆን ቀርቶ ከተጠቀሰው ቀን በኋላ የሚቀርበው የማስተካከያ ሃሳብም ሆነ ጥያቄ ተቀባይነት የሌለው መሆኑ መታወቅ ይኖርበታል።
18.መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አድራሻ ፡-አዳማ ከተማ ዳቤ ሶሎቄ ዶነጎራ ወረዳ ኦይል ሊቢያ ነዳጅ ማደያ ፊት ለፊት
- ስልክ ቁጥር፡- 022-212-4155 ወይም 09 62-17-54-34 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ።
የምስራቅ ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤት አስተዳደር
Tender details
- Deadline: 2026-06-30
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ (16) አስራ ስድስተኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-06-30 12:00
- Bid opening (note): ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ (16) አስራ ስድስተኛው የስራ ቀን 5፡00 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: የምስራቅ ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት
- Bid bond: 563,154.00 ብር
- Bid document price: 50.00 ብር
- Published: Jun 12, 2026
- Posted at: 2026-06-12T08:28:47.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.