የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ፍ/ቤት የመኖሪያ ቤትና ቦታ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ አውጥቷል

Description

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በአፈ/ከሳሽ ወ/ሮ ብዙአለም ጎሽሜ እና በአፈ/ተከሳሽ አቶ ከበደ በላይግባው መካከል ስላለው የአፈፃጸም ከስ ጉዳይ ግራ ቀኙ ባላቸው የመኖሪያ ቤትና ቦታ ላይ ለመስማማት ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ምክንያት በሞላሌ 01 ቀበሌ ልዩ ስሙ ዞን 3 ከተባለው ስፍራ አዋሳኙ ከምስራቅ ወ/ሮ አሰገደች ቤትና ቦታ ከምዕራብ አቶ አበበ የሺዳኛ ቤትና ቦታ ከሰሜን መንገድ ከደቡብ አቶ አይቸው ቤትና ቦታ መካከል የሚገኘው የቦታው ስፋት 200 ካሬ ሜትር የሆነ የመኖሪያ ዋና ቤት ፣ኩሽና መጸዳጃ ቤትና ከነ ሙሉ የቆርቆሮ አጥር ግቢውና ቦታ ከ90 ቅጠል ቆርቆሮ የተሰራ መነሻ ዋጋው ብር 1,365,658.60(አንድ ሚሊዮን ሶስት መቶ ስልሳ አምስት ሺህ ስድስት መቶ ሃምሳ ስምንት ብር ከስልሳ ሳንቲም) ሲሆን ይህንን የመኖሪያ ቤትና ቦታ ከመነሻው ዋጋው በላይ በግልፅ ጨረታ ስለሚሸጥ ሐምሌ 12 ቀን 2018 ዓ/ም ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ጨረታው ይካሄዳል፡፡ ጨረታው በሚካሄድበት ቀን ተጫራቾች ከጠዋቱ ከ4፡00-6፡00 ሰዓት ተገኝተው መጫረት ይችላሉ።

ይህንን ቤትና ቦታበ በግልፅ ጨረታ መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በቦታው ተገኝቶ ተጫርቶ መግዛት ይችላል፡፡ የጨረታው አሸናፊ አካል የሆነ ያሸነፈበትን ገንዘብ 1/4ኛውን ወዲያውኑ የሚያሲዝ ሲሆን ቀሪውን 3/4ኛውን ደግሞ በ15 ቀን ውስጥ አሟልቶ የሚያቀርብ መሆኑን አውቀው መጫረትና መግዛት የሚፈልጉ በቦታው ተገኝተው መግዛት ይችላሉ።

ማሳሰቢያ፡- ፍ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ሐራጁን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0948 306 415 / 0964 614 261 መደወል ይችላሉ።

የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ፍ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-19
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid opening: 2026-07-19 12:00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Menz Mama Meder Woreda Court
  • Published: Jun 12, 2026
  • Posted at: 2026-06-12T08:29:44.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders