የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የሚገኙ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ንብረቶች በግልፅ እና በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር38/2018
በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት የተተውና የተወረሱ እቃዎች ሽያጭ
የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የሚገኙ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በወጣው የዕቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012አንቀጽ 4(1) መሠረት
- የመገናኛ መሳሪያ ዕቃዎች
- አልባሳትና ጨርቃጨርቅ፣
- የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ፤
- የመዋቢያና የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች
- የቤትና ቢሮ፤ ዕቃዎች፣
- የተለያዩ የምግብ ነክ ዕቃዎች
- የመኪና እና
- የሞተር ሳይክል አካላትና መለዋወጫ ዕቃዎች እና
- ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች በግልፅ እና በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች(ግለሰብም ሆነ ድርጅት) ለጨረታ የቀረቡትን የዕቃዎች ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየት የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።
- ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጨራቾች በጨረታ ከሚሸጡት ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደስ ንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብርከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ በጨረታ ማስታወቂያው ላይ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡00 ፣ ከሰዓት ከ7፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት፣ ቅዳሜ ከ 2፡00 እስከ-6፡00 ሰዓት ድረስ በቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ ሂሳብና ዋስትና አስተዳደር ቡድን በአካል በመገኘት መግዛት ወይም በሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም በተከፈተው ቀጥታ አካውንት (1000174515488) የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በማስገባት hawassaawegaged (ECCH-ዕቃ አወጋገድ ሥራ ሂደት 2018) በሚለው የቴሌግራም ግሩፕ ስሊፕ በመላክ የጨረታ ሰነድ ባሉበት በቴሌግራም እንዲላክሎት ማድረግ ይቻላል።
- ያገለገለ ተሸከርካሪ/ሞተርሳይክል) ላይ መወዳደር የሚፈልግ ተጫራች ማንኛውም እድሜው ከ18 አመት በላይ የሆነ ኢትዮጲያዊ መወዳደር ይችላል።
- ተጫራቾች ለጨረታዉ ማስከበሪያ የሚሆን በሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሥም የተዘጋጀ የሚጫረቱበትን ጠቅላለ ዋጋ 5%(አምስት በመቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለትን በማሰራት የጨረታ ሰነድ እና አጠቃላይ መረጃዎችን ጨረታው ከመከፈቱ በፊት CPO በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በተጨማሪ ሀራጅ ጨረታ ለሚሳተፉ ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ የተገለፀው የጨረታ ዋስትና ( CPO) መጠን ለእያንዳንዱ ኮድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት እስከ 5ኛው (አምስተኛው) ቀን ድረስ የዕቃዎችን ናሙና ወይም ንብረቶችን በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ላይ ማየት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ6ኛው (በስድስተኛው) ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 4፡05 ፔፕሲ ፋብሪካ ፊት ለፊት በሚገኘው የሐዋሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት አዲሱ መጋዘን ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው ቦታ ተከፍቶ ጨረታው የሚጀምር ሲሆን ግልጽ ጨረታው ከተጠናቀቀ ከ10 ደቂቃ በኃላ የሀራጅ ጨረታው ይጀመራል። ነገር ግን በበዓል/እሁድ/ቀን የሚውል ከሆነ ጨረታው የሚካሄደው በተመሳሳይ ሰዓት በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታ ይሆናል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በቀረበው ቅጽ ላይ ተጫራቹ ያቀረበው ዋጋ በሚለው ርዕስ ስር በተሰጠው ክፍት ቦታ ከነ ቫቱ በጨረታ ሰነዱ ግልፅ በሆነ መልክ በመሙላት በታሸገ እንቬሎፕ ወይም ፖስታ ማቅረብ አለባቸው። ከዚህ ሰነድ ውጭ በሌላ ሰነድ ተሞልቶ የሚቀርብን ዋጋ ቅ/ጽ/ ቤቱ ለመቀበል አይገደድም።
- ማንኛውም የጨረታ ሽያጭ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም። በተጨማሪ ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኃላ በጨረታ ሰነድ ላይ የሰጠውን ዋጋ እና መግለጫ መለወጥ ወይም ማሻሻል አይችልም።
- ማንኛውም ተጫራች የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ሂደት ተጠናቆ ቅ/ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይችልም። በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO በዕለቱ የሚመለስላቸው ሲሆን አሸናፊው ያስያዘው ዋስትና ግን ከሽያጭ ጋር የሚታሰብለት ይሆናል።
- ተጫራቾች የዕቃውን ናሙና ሳያዩ ለሚሰጡት ዋጋ ምክንያት ለሚፈጠር ቅሬታ በቅ/ጽ/ቤቱ ተቀባይነት አይኖረውም።
- ለጨረታ የቀረበው ዕቃ ሽያጭ የሚፈፀመው ባለበት ሁኔታ እና በተለየው ኮድ ነው።
- አሸናፊው ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በውስጥ ማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5(አምስት) የስራ ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን ማንሳት ይኖርባቸዋል። ይህንን ባያደርጉ ጨረታው ተሠርዞ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ በማድረግ ዕቃው ድጋሜ ጨረታ ላይ የሚወጣ ይሆናል።
- ቅ/ጽ/ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁጥር፡- 046-212-5396 / 046-212-6595
በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-17
- Publishing entity: Ethiopian Customs Commission
- Bid bond: 5%
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published: Jun 12, 2026
Categories
EquipmentSafety and SecurityTextile, Garments and UniformsTextile, Garment and LeatherShoes and Other Leather ProductsEquipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsCleaning and Janitorial Equipment and ServicePersonal Care Products and ServicesFood Items and DrinksFood and BeverageSpare Parts and Car Decoration MaterialsTri Wheeler, Motorcycles and Bicycles PurchaseTelecommunication EquipmentIT and TelecomComputer and AccessoriesHome Appliance and SuppliesFurniture and FurnishingHouse FurnitureOffice FurnitureDisposal SaleSales, Disposals and ForeclosureOther SalesAmharic2merkatoEthiopian Customs CommissionSidama
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.