የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ያገለገሉ ንብረቶች ለአንድ ዓመት በሚቆይ ውል በሀገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ያገ/ን/ሽ/ግጨ/006/2018

የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ከስር በሰንጠረዥ የተገለፁትን ያገለገሉ ንብረቶች ለአንድ ዓመት በሚቆይ ውል በሀገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ተቁ

የሚሸጠው ዕቃ (አገልግሎት) አይነት

የጨረታ ማስከበሪያ መጠን

የጨረታ ሰነድ መመለሻ ቀንና ሰዓት

የጨረታ ሰነድ መክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

ሎት፡-የተቃጠለ ዘይት

በሚወዳደሩበት ሎት  የቀረበውን ጠቅላላ የመነሻ ዋጋ 10%

ሰኔ 19/2018 ዓ.ም ሰዓት 8፡00

ሰኔ 19/2018 ዓ.ም ሰዓት 8፡30

2

ሎት2፡-ያገለገለ ባትሪ

በሚወዳደሩበት ሎት  የቀረበውን ጠቅላላ የመነሻ ዋጋ 10%

ሰኔ 19/2018 ዓ.ም ሰዓት 8፡00

ሰኔ 19/2018 ዓ.ም ሰዓት 8፡30

3

ሎት3:-ያገለገለ ጎማ

በሚወዳደሩበት ሎት  የቀረበውን ጠቅላላ የመነሻ ዋጋ 10%

ሰኔ 19/2018 ዓ.ም ሰዓት 8፡00

ሰኔ 19/2018 ዓ.ም ሰዓት 8፡30

4

ሎት4፡-ባዶ በርሜል

በሚወዳደሩበት ሎት  የቀረበውን ጠቅላላ የመነሻ ዋጋ 10%

ሰኔ 19/2018 ዓ.ም ሰዓት 8፡00

ሰኔ 19/2018 ዓ.ም ሰዓት 8፡30

5

ሎት5፡-ፊልትሮ፣ አየር ማጣሪያ

በሚወዳደሩበት ሎት  የቀረበውን ጠቅላላ የመነሻ ዋጋ 10%

ሰኔ 19/2018 ዓ.ም ሰዓት 8፡00

ሰኔ 19/2018 ዓ.ም ሰዓት 8፡30

6

ሎት6፡-ቁርጥራጭ ብረት ፣ ቁርጥራጭ ካስትና ቁርጥራጭ አልሙኒየም

በሚወዳደሩበት ሎት  የቀረበውን ጠቅላላ የመነሻ ዋጋ 10%

ሰኔ 19/2018 ዓ.ም ሰዓት 8፡00

ሰኔ 19/2018 ዓ.ም ሰዓት 8፡30

7

ሎት7፡-ተረፈ ምርት(ብሮንዝ ባር ችብስ)

በሚወዳደሩበት ሎት  የቀረበውን ጠቅላላ የመነሻ ዋጋ 10%

ሰኔ 19/2018 ዓ.ም ሰዓት 8፡00

ሰኔ 19/2018 ዓ.ም ሰዓት 8፡30

 ስለሆነም በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራቾች፡-

  1. ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ማቅረብ አለበት።
  2. ለሎት አንድ የተቃጠለ ዘይት የሚወዳደር ተጫራች ከስራው ጋር አግባብነት ያለው በዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት(VAT Registration) እና የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት (TIN Certificate) ማቅረብ ያለበት ሲሆን በተጨማሪም ከአካባቢ ጥበቃ ባስልጣን የተሰጠ ህጋዊ የብቃት ማረጋጕሜ ልዩ ፍቃድ አያይዞ ማቅረብ ይኖርበታል።
  3. ተጫራቶች 22 በሚኘው ኢየሩስ ህንፃ የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ደርጅት 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 08 በመምጣት ለሺያጭ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 700.00 (ሰባት መቶ ብር) በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቅዳሜን ጨምሮ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከገዙ በኋላ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ንብረቶቹ በሚገኙበት ቃሊቲ ቅ/ፅ/ቤት የካ ቅፅ ቤት፤ ሰሚት ቅ/ፅ/ቤት፤ ሸጎሌ ቅ/ፅ/ቤት እና መካኒሳ ቅ/ፅ/ቤት በአካል በመሄድ መልከት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች በሚወዳደሩበት በእያንዳንዱ ሎት የሎቱን የጨረታ መነሻ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር በሚያያዝ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት በፊት ማስገባት ያለባቸው ሲሆን በተጨማሪም በሎት 6 ላይ ቁርጥራጭ ብረት፤ ቁርጥራጭ ካስትና ቁርጥራጭ አልሙኒየም ጨረታ ላይ አሸናፊ ተጫራች ከተለየ በኃላ አሸናፊ የሆነበትን የጠቅላላ ዋጋ 25% የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ ማሲያዝ ይኖርበታል።
  5.  የጨረታ ሳጥኑ ሰኔ 19/2018ዓ.ም ከሰዓት 8:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ሃያ ሁለት ኢየሩስ ህንፃ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር ዐ8 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የመክፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ላይ ካልሆነ (እሁድ ላይ ከዋለ ወይም በዓል ቀን ላይ ከዋለ) ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ላይ ይከፈታል።
  6. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
  7. ከሎት አንድ እስከ ሎት ስድስት ድረስ ያለው ሽያጭ በአንድ አመት ውል የሚፈፀም ሲሆን በሎት ሰባት ተረፈ ምርት(ብሮንዝ ባርችብስ) የሚሳተፉ ተጫራቾች ሽያጭ የሚከናወነው ግን ለአንድ ጊዜ ብቻ ነው።

አድራሻ፡- 22 ኢየሩስ ህንፃ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 08

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0116-663367 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።

የአዲስ አበባ ከተማ  አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-26
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-06-26 14:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa City Bus Service Enterprise
  • Bid bond: በየሎቱ በሚወዳደሩበት ሎት የቀረበውን ጠቅላላ የመነሻ ዋጋ 10%
  • Bid document price: 700.00 ብር
  • Published: Jun 13, 2026
  • Posted at: 2026-06-13T08:36:29.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders