በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በጤና ጥበቃ ቢሮ የደብረሲና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2019 በጀት አመት የሰራተኞች የትራንስፖርት ሰርቪስ አገልግሎት ግዥ፣ የህከምና ግብአቶች እና የኦክስጅን ስሊንደር ጭነት አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከሀምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2019 ዓ.ም. ለሶስተኛ ወገን በኮንትራት ለማሰራት ይፈልጋል
Description
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2019
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በጤና ጥበቃ ቢሮ የደብረሲና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2019 በጀት አመት ለሚፈፅማቸው ግዥዎች ማለትም
- ሎት1. የሰራተኞች የትራንስፖርት ሰርቪስ አገልግሎት ግዥ፣
- ሎት2. የህከምና ግብአቶች እና የኦክስጅን ስሊንደር ጭነት አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከሀምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2019 ዓ.ም ለሶስተኛ ወገን በኮንትራት ለማሰራት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት፡-
1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ሰርተፍኬት፣
2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
3. የሚያቀርቡት የንግድ ፍቃድ ዘርፍ የቫት ተመዝጋቢነት ግዴታ ለሆነባቸው አገልግሎቶች የሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ከብር 200,000.00/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
4. የጨረታ ሰነዱን ብር 150.00 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ በመክፈል ከሆስፒታሉ ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 62 መውሰድ ይችላሉ።
5. የጨረታ ማስከበሪያ በተጫራቾች መመሪያ ላይ የተገለጸውን የገንዘብ መጠን ለሆስፒታሉ በCPO /በጥሬ ገንዘብ/ ማስያዝ አለባቸው።
6. የቅድሚያ ግብር ዊዝሆልዲንግ ክፍያ ከብር 10,000.00/አስር ሺህ ብር/ በላይ አገልግሎቶች 3% የሚቆረጥ ይሆናል።
7. ለሰራተኞች ትራንስፖርት ጨረታ ተሽከርካሪው በወንበር 24/ሀያ አራት/ ሰው እና በላይ የመጫን አቅም ያለው፡፡ እና የተሽከርካሪው የስሪት ዘመን እንደ ኤሮፓ አቆጣጠር 2010 እና ከዚህ ወዲህ የተመረተ።
8. ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ ለመኪናው የሚያስፈልጉ ሙሉ ወጪዎችንና ናፍጣ በራሱ የሚሸፈን መሆኑን ታሳቢ አድርጎ ይሆናል።
9. ለሰራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ጨረታ ለሚሳተፉ ተጫራቾች የስራ ጊዜው በመንግስት የስራ ሰዓት መግቢያና መውጪያ/ጠዋት፣ምሳ ሰዓትና ማታ/ አገልግሎት መስጠት ሲሆን ለጭነት አገልግሎት ጨረታ ደግሞ ጭነት በሚኖርበት ጊዜ ብቻ ይሆናል።
10. የተሽከርካሪው ሊብሬ በተጫራቹ ስም የሆነ፣ኢንሹራንስ እና ሶስተኛ ወገን የተገባለት፣የቴክኒክ ምርመራ /ቦሎ/ ያሰራ መሆን አለበት።
11. ለሰራተኞች የትራንስፖርት መኪናው በህዝብ ትራንስፖርት እና ለጭነት አገልግሎት በደረቅ ጭነት አገልግሎት የተመዘገበ መሆን አለበት።
12. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ሙሉ ስማቸውን፣ፊርማቸውንና የድርጅታቸውን ማህተም ማስቀመጥ አለባቸው።
13. የጨረታዎቹ አሸናፊ ሆነው የተመረጡ ድርጅቶች ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በCPO /በጥሬ ገንዘብ/ ለሆስፒታሉ እዲያሲዙ ሲጠየቁ በማስያዝ ውል መውሰድ ይኖርባቸዋል።
14. የሁለቱም ውለታዎች እንደ አስፈላጊነቱ በሩብ አመት፣በግማሽ አመት ወይም የአንድ በጀት አመት ውል የሚፈፀም ይሆናል።
15. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ በትክክል ነጣላ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋውን በመሙላት ዝርዝር አባሪ ዶክሜንቶችን ጨምሮ የጨረታ ሰነዱን ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በፖስታ አሽገው ማስገባት ይኖርባቸዋል።
16. ጨረታው ከፍት ሆኖ የሚቆየው ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ይታሸግና ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ በሆስፒታሉ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች(ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው የሚከፈት ይሆናል።
17. ለሁለቱም ሎቶች ተጨማሪ መረጃዎችን ከጨረታው መመሪያና ከዋጋ መሙያ ላይ ማየት ይቻላል።
18. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የመንግስት የስራ ቀን ካልሆነ/ ዝግ ከሆነ በቀጣይ ባለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል።
19. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
20. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0913 869 679 ፣ 0925 402 088 ወይም 0924 854 239 ደውለው ይጠይቁ።
አድራሻ፡- ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ በሚወስደው ዋና መንገድ ላይ 190 ኪሎ ሜትር ደብረሲና ከተማ
የደብረሲና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
Tender details
- Deadline: 2026-06-29
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-06-29 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Debre Sina Elementary Hospital
- Buyer address: ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ በሚወስደው ዋና መንገድ ላይ ደብረሲና ከተማ 190 ኪሎ ሜትር
- Bid document price: 150.00 ብር
- Published: Jun 13, 2026
- Posted at: 2026-06-13T08:45:36.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.