በድሬዳዋ አስተዳደር የድልጮራ ሆስፒታል በ2018 ዓ.ም. ለሆስፒታሉ ያገለገሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ድ/ዳ/ድ/ጮ/ሆ/12/18

በድሬዳዋ አስተዳደር የድልጮራ ለሆስፒታሉ በ2018 ዓ.ም. ለሆስፒታሉ ያገለገሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

በዚሁ መሠረት በጨረታው ላይለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

1. እንድ ተጫራች ጨረታ ሠነድ በሚገዛበት ጊዜ የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ ካርድ አቅርቦ ሰነድ መግዛት ይችላል።

2. የሽያጭ ፈጻሚው አካል ባወጣው ጨረታ ምክንያት የተቀበላቸውን ከተጫራቾች የሚቀርቡ የመጨረቻ ሰነዶችን በባለቤትነት የመያዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። በመሆኑም ዘግይተው የደረሱ ጨረታዎች ካልሆኑ በስተቀር ተጫራቾች ያቀረቡት የመጨረቻ ሰነድ እንዲመለስላቸው የመጠየቅ መብት አይኖራቸውም።

3. አንድ ተጫራች ጨረታ በሚያቀርብበት ጊዜ በጨረታ ሰነዱ የተመለከቱትን የሽያጭ ሥነ ስርዓቶችና ሁኔታዎች ያለምንም ገደብ እንደተቀበለ ይቆጠራል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች ጨረታ ከማቅረባቸው በፊት በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተመለከቱትን ዝርዝር መስፈርቶች በጥንቃቄ ሊመረምራቸው ይገባል።

4. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል በድል ጮራ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር A/02 በመቅረብ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ።

5. መስፈርቱን የሚያሟላ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር CPO እና በጥሬ ብር ብቻ ነው።

  • ሎት 01-የህክምና መ/መሳ/....... CPO 20,000.00 (ሃያ ሺ ብር)
  • ሎት 02 ወረቀቶች ……..CPO 20,000.00 (ሃያ ሺ ብር)
  • ሎት 03 የመኪና ዕቃዎች……..10,000.00 (አስር ሺ ብር)
  • ሎት 04- የTV computer and Electronics CPO ......10,000.00 (አስር ሺ ብር)

ጨረታው ኦርጅናል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

6. ተጫራቾች የጨረታሠነዱን በሰም በታሸገ ኤንቨሎኘ በማድረግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ መቀበያ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

7. የጨረታ ሰነዱ የሚከፈትበት ቀን ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የስራ ቀናት ከቆየ በኋላ በ16ኛው ቀን ጠዋት 4:00 ሠዓት ተዘግቶ ከቀኑ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆስፒታሉ ግዢ ፋ/ን/አስ ዳይሮክትሬ ቢሮ ቁጥር 155 ይከፈታል።

8. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሁፍ እንደተገለፀለት አስፈላጊውን የጨረታ ውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከሆስፒታሉ ጋር ውል መፈራረም አለበት፡፡ ይህ ባይፈፀም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።

9. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፤ሙሉ አድራሻቸውን እና ፊርማቸውን እንዲሁም የተሟላ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።

10. ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት በኋላ የሚደርሱ የመጨረቻ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።

11. አንድ ተጫራች አንድ መደብ ወይም ከአንድ በላይ መደብ (በመለያ ቁጥሮች) የተጠቀሱትን ልዩ ልዩ ሎቶች ዕቃዎችን መጫረት ይችላል።

12. የጨረታው አሸናፊድርጅት ወይም ግለሠብ ጨረታው ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ 05(አምስት) የስራ ቀኖች ውስጥ እቃዎቹን ማንሳት ይኖርበታል:: በተጠቀሠው ቀን ካላነሡ በየቀኑ 1,000.00(አንድ ሺህ) ብርታስቦ ለሆስፒታሉ ከ05(አምስት)ቀን ውስጥ ካላነሳ ከዚያ በኋላ ሲፒኦ ለመንግስት ገቢ ሆኖ ወደ ሁለተኛው የጨረታ አሸናፊ ይዞራል::

13. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ወይም ግለሠብ ጨረታው አንድ ሎት ሲያሸንፍ በሰሩ የተጠቀሠውን በቁጥርብዛት በጨረታ ሠነዱ ላይ የተጠቀሰውን መጠን ብቻ ሳይሆን የቀረበውን መጠን በሙሉ ባሸነፈበት ዋጋ መውሰድ ግዴታ አለበት።

14. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ:- በድሬዳዋ አስተዳደር የድል ጮራ ሆስፒታል

ስልክ ቁጥር 0982 540 408 / 0901 103 211 /2-521 115 693

ፖስታ ሳጥን ቁጥር 177

ድል ጮራ ሆስፒታል


Tender details

  • Deadline: 2026-07-02
  • Publishing entity: Dire Dawa Dil Chora Hospital
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published: Jun 14, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders