ፀደይ ባንክ አ.ማ. ንብረቶች ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የኃራጅ
ሽያጭ ማስታወቂያ

ፀደይ ባንክ አ.ማ. ለአቶ ጌታቸዉ አባት ለሰጠዉ ብድር በመያዣ የያዛቸዉንና ዝርዝር ሁኔታቸዉ ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የገለጹትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልፅ ጫረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

.

የተበዳሪ ስም

የንብረት አስያዥ ስም

የንብረቱ መገኛ ደረጃና ካርታ ቄጥር

የጫረታዉ መነሻ ዋጋ

1

አቶ ጌታቸዉ አባት

አቶ ጌታቸዉ አባት

በአ/ ከተማ ቦሌ /ከተማ ወረዳ 12 ካርታ ቁጥር ቦሌ 12/40/4/1/20892/10731/01 B+G+3 መኖሪያ ቤት

29,547,213.39

 

2

አቶ ጌታቸዉ አባት

/ ቤዛ ጌታሁን

 

በአ/ ከተማ የካ /ከተማ ወረዳ 05 ካርታ ቁጥር የካ/253124/13 B+G+3 መኖሪያ ቤት

64,510,456.93

 

3

አቶ ጌታቸዉ አባት

ጂኤኤ የጨዉ ማቀነባበሪያ /የተ/የግ/ ማህበር

በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ የካርታ ቁጥር // //10/9/14 ድርጅት

35,302,143.8

 

በመሆኑም ተጫራቾች ለጫረታ ከመቅረባቸዉ በፊት የሚከተሉትን ደምቦች በመገንዘብና ቅድመ ሁኔታዎችን በማሟላት ተጫራቾች እንዲጫረቱ ይጋብዛል።

1. ተጫራቾች የቤቱን ጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 1/4 (በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲ.ፒ.ኦ) በጸደይ ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት ለጫረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

2. የጫረታዉ አሸናፊ አሸናፊነቱ የሚረጋገጠዉ የጫረታዉ ዉጤት በሚመለከተዉ አካል ጸድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠዉ ብቻ ይሆናል።

3. በጫረታዉ የሚሳተፈዉ በህግ ሰዉነት ያገኘ ከሆነ የድርጅቱ መመስረቻ ጽሁፍ ወይም መተዳደሪያ ደምብ፤ ህጋዊ ሰዉነት ያገኘበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ህጋዊ ዉክልና ማቅረብ አለበት።

4. የጫረታዉ አሸናፊ አሸናፊነቱ በባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ10 ቀናት ዉስጥ አጠቃሎ መክፈልና በጫረታ ያሸነፈዉን ንብረት መረከብ ይኖርበታል:: አሸናፊዉ በ10 ቀናት ዉስጥ ገንዘቡን ካልከፈለ ጨረታዉ ተሰርዞ ለጨራታ ማስከበሪያ ያስያዘዉ ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።

5. በጫረታዉ ለተሸነፉ ተጫራጮች ያስያዙት ጥሬ ገንዘብ ወይም ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል።

6. የጫረታ አሸናፊዉ ከሚገዛዉ ንብረት ዋጋ በተጨማሪ ከቤቱ ጋር የተያያዙ ማናቸዉም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፡ ግብር፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ 15% እና ከስም ዝዉዉሩ ጋር የሚገናኙ ማንኛዉንም ወጭዎች ገዢ ይሸፍናል/ ይከፍላል:: ዉዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሆኖ ለቀረዉና የክፍያ ጊዜዉ ላልደረሰ የሊዝ ክፍያ ገዢ ከሚመለከተዉ የመንግስት አካል ጋር እንዲዋዋል ይደረጋል።

7. ተጫራቾች ቤቱን /ድርጅቱን/ በባንኩ አማካኝነት መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ።

8. ጫረታዉ የሚካሄደዉ ሀምሌ 2/2018 ከጠዋቱ 3.00---5.00 የተጫራቾች ምዝገባ፤ ከ5.00 እስከ ቀኑ 6.00 ሰዓት ጫረታ በአዲስ አበባ ከተማ በልደታ ክ/ከተማ ልዩ ቦታዉ ሰንጋ ተራ በባንኩ ዋና መ/ቤት 11ኛ ፎቅ ይሆናል።

9. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጫረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።

ለተጨማሪ መረጃ፡- ፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት በስ.ቁ +251918779825 ደዉሎ መጠየቅ ይቻላል።


Tender details

  • Deadline: 2026-07-09
  • Bid closing time: 11:00
  • Bid opening: 2026-07-09 11:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Tsedey Bank S.C.
  • Buyer address: Legahar Orda Building, 8th Floor room No-804
  • Bid bond: 25%
  • Published: Jun 14, 2026
  • Posted at: 2026-06-15T12:11:52.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders