በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዋግ ኸምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ የተለያዩ አይነትና መጠን ያላቸውን የጽህፈት መሣሪያ፣ የተሽከርካሪ ጎማ እና የህንጻ መሳሪያ ግዥ እንዲሁም የአዳራሽ ወንበር ጥገና አገልግሎት ግዥ በሀገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ሀገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዋግ ኸምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለብሄረሰብ አስተዳደሩ የተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አይነትና መጠን ያላቸውን የጽህፈት መሣሪያ፣ የተሽከርካሪ ጎማ እና የህንጻ መሳሪያ ግዥ እንዲሁም የአዳራሽ ወንበር ጥገና አገልግሎት ግዥ በሀገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፤

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2. ከሚገዛው እቃ ጋር የተዛመደ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርትፍኬት (Value Added Tax Certificate) ተመዝጋቢ ከሆኑ የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት (Tax Payer Identification Number) እንዲሁም ሌሎች ለጨረታው የሚጠቅሙ ማስረጃዎችን የተገናዘበ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል የምትችል።

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት ምድብ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 ማግኘት ይችላል።

4. ተጫራቾች በሌላ ዋጋ ተመስርቶ መወዳደር የማይቻል መሆኑንና የጨረታ ማስከበሪያ ጸንቶ  ዋስትናው አሸናፊው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 20 ቀናት እንዲሁም የውል ማስከበሪያ ዋስትናው ውሉ ከተፈረመበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 30 ቀናት ጸንቶ ሊቆይ የሚችል መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ዋናውን የገቢ ደረሰኝ ከመወዳደሪያ ሃሳቡ ጋር አብሮ ማስገባት ሲኖርባቸው በጨረታ ሰነዱ ከተቀመጠው ዝርዝር መግለጫ ውጭ መጨመርም ሆነ መቀነስ አይፈቀድም።

6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱ ጨረታ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን አንስቶ እስከ ተከታታይ አስራ አምስተኛው ቀን ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ሰነዱን በመግዛት የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ አንድ ወጥ ፖስታ ዋናውን በዋ ኸ/ብ/አስ/ር ገንዘብ መምሪያ ግዥ/ን/አስ/ር/ቡድን ቢሮ ቁጥር 9 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በአስራ ስድስተኛው ቀን 3፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋ/ኸ/ብ/አስ/ር/ገንዘብ መምሪያ ግዥ/ን/አስ/ር/ደ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 9 ጨረታው በጋዜጣ ከታወጀበት ጊዜ አንስቶ በአስራ ስድስተኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡00 ይከፈታል።

8. ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሃሳባቸውን ለማሻሻል ወይንም ከጨረታ ለመውጣት የፈለጉ እንደሆነ የጨረታ መወዳደርያ ሃሳብ ለማቅረብ ከተሰጣቸው አምስት ቀን በፊት በጽሁፍ ሊያሳውቁ ይገባል።

9. መምሪያው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ይህም ሲባል ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታ ለመወዳደር ላወጡት ወጭ መ/ቤቱ ሃላፊነት የማይወስድ መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

10. ተጫራቾች ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በዋ/ኸ/ብ/አስ/ር/ገ/ኢ/ት መምሪያ ግ/ን/አስ/ር/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 9 በአካል በመገኘት ወይንም በስልክ ቁጥር 033 440 1230/ 024 900 62 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

በአ/ብ/ክ/መ የዋግ ኸምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር መምሪያ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-30
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን አንስቶ በአስራ ስድስተኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30
  • Bid opening: 2026-06-30 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን አንስቶ በአስራ ስድስተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: ANRS Wag Hamra National Administration FEDB
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 100.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published: Jun 15, 2026
  • Posted at: 2026-06-16T07:46:58.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders