የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
Description
የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
በምዕራብ ጎጃም ዞን የፍኖተ ሰላም ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት በ2018 በጀት አመት ለ3ኛ ጊዜ የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 በፊደል ተራ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት ለመኖሪያ እና ለሆቴል አገልግሎት የሚውሉ የተዘጋጁ ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ለመጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ግለሰብ ከሰኔ 09/2018 ዓ.ም ጀምሮ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ ለመኖሪያ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ለሆቴል ብር 400 (አራት መቶ ብር) የማይመለስ በመክፈል እና የጨረታ ሰነድ ማስከበሪያ (ሲፒኦ) 35 በመቶ በማስያዝ በከተማ አስተዳደሩ ቅጥር ግቢ ቢሮ ቁጥር 76 ድረስ በመምጣት ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
1. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ከሰኔ 09/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 22/2018 ዓ/ም 11፡00 ብቻ ይሆናል፡፡
2. ጨረታው የሚዘጋው ሰኔ 22/2018 ዓ.ም በ11፡00 ይሆናል፡፡
3. ቦታውን መጎብኘት ለሚፈልጉ ተጫራቾች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገለጸው መርሀ-ግብር መሰረት ይሆናል፡፡
4. ጨረታው የሚከፈተው ሰኔ 23/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 በከተማ አስተዳደሩ ቅጥር ግቢ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡
5. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
6. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በስልክ ቁጥር 058 775 08 13 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የፍኖተ ሰላም ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-29
- Bid closing time: 17:00
- Bid opening: 2026-06-30 09:00
- Region: Amhara
- Publishing entity: Finote Selam City Administration City Development Housing Construction Services Bureau
- Bid bond: 35 በመቶ
- Bid document price: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Published: Jun 15, 2026
- Posted at: 2026-06-16T11:21:05.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.