የሆሣዕና ማረሚያ ተቋም 44 እና ተሳፋሪዎችን የመጫን አቅም ያለው መካከለኛ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የመኪና ኪራይ ትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል
Description
ለመኪና ትራስፖርት አገልግሎት ኪራይ የወጣ
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ሆማተ/227/2018
የሆሣዕና ማረሚያ ተቋም የህግ ታራሚዎችን እና የፖሊስ ሰራዊቱንና ሠራተኞቹን ተቋሙ ባዘጋጀው የድርጊት መርሃ ግብር መሠረት በየቀኑ ከጧቱ 12፡30-11፡30 ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ ድረስ የሚያመላልስ እንዲሁም ከመደበኛ ሰርቪስ ሥራዎች በተጨማሪ ቅዳሜ፤ እሁድና የበዓል ቀናት እንደአስፈላጊቱ ጥሪ ሲደረግ መጥቶ አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን በመገንዘብ፤ ከተማው ወደ ማረሚያ ተቋም ድረስ ከ07 ኪ/ር ደርሶ መልስ ሰርቪስ አገልግሎት ሊሰጥ የሚችል፤ ከዚህ በታች በሠንጠረዡ ውስጥ የተመለከተውን መካከለኛ የህዝብ ማመላለሻ የትራንስፖርት አገልግሎት፤ መስፈርቱን ከሚያሟሉ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን /ግለሰቦችን/ ከሀምሌ 1/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 30/2019 ዓ/ም ድረስ ለስድስት ወራት በሚቆይ የማዕቀፍ ስምምነት፤ በውል ሰጪና በውል ተቀባይ መካከል በሚደረገው የውል ስምምነት መሠረት የሰርቪስ የአገልግሎት ጊዜውን እንደአስፈላጊነቱ ከ01 ወር እስከ 06 ወራት ተጨማሪ ጊዜ ለማራዘም እንደሚቻል ታሳቢ ባደረገ መልኩ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የመኪና ኪራይ ትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የአገልግሎቱ/አይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
|
01 |
44 እና ተሳፋሪዎችን የመጫን አቅም ያለው መካከለኛ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ |
በቁጥር |
01 |
መመዘኛ መስፈርቶች፣
1. በመስኩ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ፤የንግድ ምዝገባ ምስክር ወቀረት፤የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፤ የVAT 15% ምዝገባ ማስረጃ፤ የባለቤትነት ማረጋገጫ መታወቂያ (ሊብሬ)፤ የብቃት ማረጋገጫ ሰርትፍኬት፤ እንዲሁም የ3ኛ ወገን ኢንሹራንስ፤የመልካም ሥራ አፈጻጸም ሰርትፍኬት ያለው/ላት፤ እንዱሁም የዘመኑን ግብር የከፈለሰች፤
2. ተጫራቾ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ሆሣዕና ማረሚያ ተቋም ግዥና ፋይናንስ ንብ/አስ/የሥራ ሂደት ቢሮ በመቅረብ ለዚሁ ግዥ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በነፃ መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ የጨረታ ማስከበሪያን በሚመለከት የብር 7,000/ሰባት ሺህ /ብቻ CPO ዋስትና ሰነድ በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
3. ተጫራቶች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አሥር) ተከታታይ ቀናት ውስጥ የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ተሞልቶ ከሙሉ ሰነዶች ጋር እንዲሁም ከላይ በተራ ቁጥር (01) ላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒዎች ጋር በታሸገ ኤንቬሎፕ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የንግድና ሌሎች ኮፒ ማስረጃዎች ላይ አጠራጣሪ ነገሮች ከታዬ ኦርጅናል ማስረጃዎችን አስቀርቦ የመጣራት እና የማረጋገጥ የተቋሙ ኃላፊነት ሆኖ ተጫራቾቸቹም ኦርጅናል ማስረጃዎችን የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
5. ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች /ህጋዊ/ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት በማረሚያ ተቋሙ ግዥና ፋይናንስ/ ንብረት አስተዳደር ቢሮ ወይም ተመሳሳይ አዳራሽ የሚከፈት መሆኑን ስንገልጽ፤ ዕለቱ የበዓላት /የዕረፍት/ ቀን ከሆነ በማግስቱ በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
6. ተወዳደሪያዎች በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይቻሉም፤
7. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፍል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 26 20 08 23 ወይም 09 12 05 28 32 ደውሎ መጠየቅ ይችላል።
የሆሣዕና ማረሚያ ተቋም
Tender details
- Deadline: 2026-06-26
- Publishing entity: Hossana Correctional Facility
- Bid bond: 7,000.00 ብር
- Published: Jun 17, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.