የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ሕግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ሕግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት በቀን 17/10/2018 ዓ/ም እና 20/10/2016 በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቶች የጨረታ ሰነዱን በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት መግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሥም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት በተጫራች ስም የማይመለስ 100(መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክሎት በማድረግ ለጨረታ የቀረቡትን የእቃዎችን ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየትና እና በማረጋገጥ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች በሟሟላት በጨረታው መሳተፍ የሚቻል ሲሆን እቃዎችን ሳምፕል ከቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ፡ ከአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት፡እና በቴሌግራም ማየት የሚቻል መሆኑንና ወደ ቃሊቲ እንዲመጣልዎት የምትፈልጉት የእቃ ሳሙና ካለ የጨረታ ማስታወቂያ በወጣበት ቀን በስልክ ቁጥር 022-224-1402 በመደወል ወደ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት እንዲመጣልዎት ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
የጨረታ መስፈርቶች ፡-
- ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚያስፈልግ ተጫራች በጨረታ በሚሸጡ ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርትፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለ መሆኑ ክሊራንሰ (Clearance) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅሰቃሴያቸውን ለታክስ ማዕከሉ ያሳወቁበት፣ በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምሰክር ወረቀት እና የመለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል።
2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዘውትር በሥራ ሰዓት እስከ ቀን 17/10/2018 ዓ/ም እና 20/10/2018 ባሉት ቀናት ግልፅ እስከ ጠዋቱ 3፡45 እንዲሁም ለሃራጅ ጨረታ በዚሁ ቀን እስከ ረፋዱ 5፡00 የእቃውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ አዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት በአካል በመገኘት በግዞት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር / በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት በቴሌግራም እንዲላክሎት ማድረግ ይችላሉ።
3. ለግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) የሚወዳደሩበት እቃ ኮድ 5% እንዲሁም ለሃራጅ ጨረታ ለሚ ወደሩበት እቃ ኮድ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ አሰርተው በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
4. ተጨራቾች በሚከተለውየጨረታ ቀናት (እስኬጁል) መሰረት በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በመገኘት መጫረት ይችላሉ።
|
የጨረታ ቦታ
|
የጨረታ ዓይነት
|
ለጨረታ የቀረቡ እቃዎች
|
የዕቃዎች መመልከቻ ቀን ከወጣበት ቀን ጀ ምሮ እስከ |
የጨረታው የመዝጊያና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
ቃሊቲ ጉምሩክ
|
ግልፅ እና ሃራጅ
|
ጫማዎች፣ አልባሳት፡ ኮስሞቲክስ፡የመኪናመለዋጫ፡ ኤሌክትሪክእቃዎች፣ ተሽከርካሪመኪናዎች፣ የሞባይል ቀፎና አክሰሰሪ፡ ምግብ ነክ፣ እና ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎች |
ለግልፅ ጨረታ እስክ 17/10/18 እሮብ እና 20/10/18 ቅዳሜ ከጠዋቱ 3፡45 እና ለሃራጅ ጨረታ እስከ 4፡45 |
ለግልፅ ጨረታ 17/10/18 እና 20/10/2018 ከጠዋቱ 3፡45 እና ለሃራጅ ጨረታ እስከ 5፡00 |
5. የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡በቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።
6, ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋሰትና ያስያዙት (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ 3 የሥራ ቀናት ውሰጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
7. ከአሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ3 ቀናት ውሰጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን በመረከብ ከመጋዝን ማውጣት ይኖርበታል።
8. ከላይ በተ.ቁ 7 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለኮሚሽኑ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሜ ለሽያጭ ይቀርባል።
9. ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ለተጨማሪ መረጃ በሰልክ ቁጥር፡- 022-224-1402 ደውለው ስለጨረታው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ።
በጉምሩክ ኮሚሽን የአዋሽ ቅ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-27
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-06-27 12:00
- Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
- Region: Oromia
- Publishing entity: Ethiopian Revenue & Customs Authority Awash Branch
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 100 (አንድ መቶ ብር)
- Published: Jun 17, 2026
- Posted at: 2026-06-17T07:41:01.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.