በላይነህ ክንዴ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ በተለያዩ የግንባታ ፕሮጀክት ሳይቶች የሚገኙ የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን፤ እንጨት እና ግንባታ ተረፈ ምርቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ፈልጋል

Description

 የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ

ድርጅታችን በላይነህ ክንዴ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ በተለያዩ የግንባታ ፕሮጀክት ሳይቶች የሚገኙ

  • የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን፤
  • እንጨት እና
  • ግንባታ ተረፈ ምርቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ፈልጋል።

 ስለሆነም የሚሸጡ የግንባታ ቁሳቁሶች በሚከተለው ሠንጠረዥ መመልከት እና መጫረት ይቻላል፡-

.

የዕቃው ዓይነት

የሚገኝበት ሳይት

መለኪያ

ብዛት

የሚገዙበት ዋጋ (ብር)

ነጠላ

ጠቅላላ

1

ቁርጥራጭ አርማታ ብረት

ፍላሚንጎ ሳይት

.

50,000

 

 

2

ያገለገለ እና ጥሩ ይዞታ ያለው የከባድ መኪና ጎማ

ፍላሚንጎ ሳይት

ቁጥር

302

 

 

3

ያገለገለ እና ጥሩ ይዞታ ያለው የከባድ መኪና ጎማ

ገላን ሳይት

ቁጥር

217

 

 

4

ያገለገለ እና ጥሩ ይዞታ ያለው የቀላል መኪና ጎማ

ፍላሚንጎ ሳይት

ቁጥር

18

 

 

5

ያገለገለ እና ጥሩ ይዞታ ያለው የማሽነሪ መኪና ጎማ

ገላን ሳይት

ቁጥር

20

 

 

6

የተለያዩ የመኪና እና የማሽነሪ ባትሪዎች

ፍላሚንጎ ሳይት

ቁጥር

7

 

 

7

የተለያዩ የመኪና እና የማሽነሪ ባትሪዎች

ገላን ሳይት

ቁጥር

51

 

 

8

የተለያዩ የመኪና መለዋወጫዎች

ፍላሚንጎ ሳይት

ቁጥር

30

 

 

9

የባህር ዛፍ እንጨት ቁርጥራጮች

ፒያሳ ሳይት

ቢያጆ

4

 

 

10

የሞራሌ እና ጣውላ ቁርጥራጮች

ፒያሳ ሳይት

ቢያጆ

10

 

 

በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው ነጋዴዎች ወይም ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡-

  1. የዘመኑ ግብር የተከፈለበት የታደሠ ንግድ ፈቃድ ሰርቲፊኬት ኮፒ፤
  2. የንግድ ምዝገባ ሰርቲፊኬት (ቲን ነምበር) ኮፒ፤
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርቲፊኬት (ተመዝጋቢ ከሆኑ) ኮፒ፣
  4. የሚያቀርቡት ዋጋ 10 ፐርሰንት ጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) በጥሬ ገንዘብ፤ በቼክ ወይም ባንክ በተመሰከረለት ሲ.ፒ.ኦ፤
  5. ለብቻ በአነስተኛ ፖስታ በሰም የታሸገ ዋጋ ማቅረቢያ ወይም ፕሮፎርማ ኢንቮይስ
  6. ከላይ የተጠቀሱት ማስረጃዎች እና ሌሎችም ተወዳዳሪዎች ለውድድር ይጠቅመኛል የሚሏቸው ማስረጃዎች መቅረብ አለባቸው።

ተጫራቾች ዕቃዎችን በፕሮጀክት ሳይቶች በመቅረብ ማየት ይችላሉ። ከላይ የተጠቀሱት ሁሉም ማስረጃዎች በትልቅ ፖስታ ውስጥ በሰም ታሽገው እና ማህተም አርፎባቸው መቅረብ እና አራት ኪሎ፤ አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ህንጻ የምድር ወለል በሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ እስከ ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን አስመዝግበው እስከ ጥዋቱ 4፡00 ሰዓት ማስገባት አለባቸው።

የጨረታ ሳጥኑ ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጥዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። አሸናፊዎች ጨረታውን ማሸነፋቸውን ድርጅቱ ከአሳወቀ ጀምሮ ባሉት አምስት ተከታታይ ቀናት ውስጥ ትራንስፖርት አቅርበው ዕቃዎችን ማንሳት ይጠበቅባቸዋል። በተሰጠው የጊዜ ገደብ ካላነሱ ድርጅቱ ለሚደርስ ጥፋት ተጠያቂ አይሆንም።

ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም።


Tender details

  • Deadline: 2026-06-22
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-06-22 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: በላይነህ ክንዴ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ
  • Bid bond: 10%
  • Published: Jun 17, 2026
  • Posted at: 2026-06-17T08:03:53.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders