ሕብረት ባንክ አ.ማ. በባንኩ ዋና መ/ቤት፣ አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙ ዲስትሪክቶች ቅርንጫፎች ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች (ፈርኒቸሮች) ለሁለት ዓመት በሚቆይ የኮንትራት ውል የጥገና አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ሕባ/036/2018
ሕብረት ባንክ አ.ማ. በባንኩ ዋና መ/ቤት፣ አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙ ዲስትሪክቶችና ቅርንጫፎች ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች (ፈርኒቸሮች) ለሁለት ዓመት በሚቆይ የኮንትራት ውል የጥገና አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል።
ስለሆነም የቢሮ ዕቃዎች ጥገና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት የጨረታ ሰነዱን ገዝተው የመጫረቻ ሰነድ/ፕሮፖዛል ሊያቀርቡ ይችላሉ።
1. ተጫራቾች ይህ ጨረታ ለመጀመሪያ ጊዜ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማለትም ከሰኔ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ግዥ ዋና ክፍል ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ራስ አበባ አረጋዊ መንገድ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ንግድ ስራ ኮሌጅ ት/ቤት ፊት ለፊት የማይመለስ ብር 230.00 (ሁለት መቶ ሰላሳ) በአቅራቢያዎ በሚገኙ የሕብረት ባንክ ቅርንጫፍ በሂሳብ ቁጥር IN0403007 በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
2. የጨረታ ሰነዱን የባንኩ ዋና መ/ቤት በሚገኝበት ግዥ ዋና ክፍል ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ራስ አበባ አረጋዊ መንገድ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ንግድ ስራ ት/ ቤት ፊት ለፊት ህብር ታወር 19ኛ ፎቅ ግዥ ዋና ክፍል በመገኘት መውሰድ ይቻላል።
3. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን ሞልተው ከማስገባታቸው በፊት የጨረታ ሰነዱ ላይ የተካተተውን የተጫራቾች መመሪያ በደንብ ማየት ይኖርባቸዋል።
4. እያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ መቅረብ አለበት።
5. ተጫራቾች እስከ ሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ.ም. 8፡00 ሰዓት ድረስ የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ሕብረት ባንክ አ.ማ. ዋና መ/ቤት ግዥ ዋና ክፍል ህብር ታወር 19ኛ ፎቅ ማስገባት ይችላሉ።
6. ጨረታው በዕለቱ ሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ.ም. 8፡30 በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 19ኛ ፎቅ ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
7. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከህብረት ባንክ ውጭ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
ስልክ ቁጥር 011-470 6541 ወይም +251 11 467 3208
ሕብረት ባንክ
Tender details
- Deadline: 2026-07-01
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-07-01 14:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Hibret Bank S.C.
- Bid document price: 230.00 (ሁለት መቶ ሰላሳ ብር)
- Published: Jun 17, 2026
- Posted at: 2026-06-17T08:29:25.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.