ኢንተርናሽናል የልብና ልብ ነክ ደዌዎች ሕክምና ማዕከል አክሲዮን ማኅበር ያገለገሉ የተለያዩ የሕክምና መገልገያ መሳሪያዎችን ማለትም የኤሌትሪክ አልጋዎች፣ የቀዶ ጥገና አልጋና መብራት፣ አልትራሳውንድ ማሽን፣ የአንስቴዥያ ማሽን፣ የአውቶ ክሌቭ ማሽን ወዘተ በግልፅ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡ ICMC /Lo/ H/004/2018/2026

ኢንተርናሽናል የልብና ልብ ነክ ደዌዎች ሕክምና ማዕከል አክሲዮን ማኅበር ያገለገሉ የተለያዩ የሕክምና መገልገያ መሳሪያዎችን ማለትም የኤሌትሪክ አልጋዎች፣ የቀዶ ጥገና አልጋና መብራት፣ አልትራሳውንድ ማሽን፣ የአንስቴዥያ ማሽን፣ የአውቶ ክሌቭ ማሽን ወዘተ በግልፅ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትጫረቱ ተጋብዟችኋል።

1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈላችሁ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሠነድ ማቅረብ የሚትችሉ ሆኖ የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታ ዋስትና በሚያስገቡት ጠቅላላ ዋጋ ከቫት በፊት 2% (ሁለት በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ በአይ ሲ ኤምሲ አጠቃላይ ሆስፒታል (INTERNATIONAL CARDIO VASCULAR MEDICAL CENTRE SHARE COMPANY) ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ማሰያዝ ይኖርባቸዋል። ለዚህም ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበትን ጊዜ እና ተጨማሪ 28 ቀናትን የሚሸፍን ሆኖ መቅረብ አለበት።

2. ተጫራቾቹ ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ሰነዱን ለየብቻ ለይቶ ማቅረብ ይኖርበታል።

3. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) የስራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ይዘጋል። በዚሁ ዕለትም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 3ኛ ፎቅ ላይ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።

4. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል።

5. ጨረታው የሚፀናበት ጊዜ 60 (ስልሳ) የስራ ቀናት ስለሆነ ተጫራቾችም ይህንኑ አውቀው ስለመቀበላቸው በኦርጅናል ቴክኒካል ሰነዳቸው ላይ ማረጋገጥ አለባቸው።

6. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም። ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፀሀይ ሪል እስቴት ጀርባ

ለበለጠ መረጃ፦ በስልክ ቁጥራችን +251 91 287 3173 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

አይ ሲ ኤምሲ አጠቃላይ ሆስፒታል


Tender details

  • Deadline: 2026-07-04
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) የስራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-07-04 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) የስራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 5፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: International Cardiovascular Medical Center Share Company
  • Buyer TIN: 0001228470
  • Bid bond: 2%
  • Published: Jun 17, 2026
  • Posted at: 2026-06-17T09:36:59.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders