የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የሠራተኞች የካፍቴሪያ አገልግሎት ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር 003/2018

የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት የተለያዩ ሎቶች ላይ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት፡-

ሎት 1፡ የሠራተኞች የካፍቴሪያ አገልግሎት

  1. በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች አሟልተው በጨረታው መወዳደር ይችላሉ። የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት፣የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና ክሪላንስ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም አቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፣
  3. በተዛማጅ አገልግሎት ቢያንስ 2 /ሁለት/ ዓመት የስራ ልምድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. ከወጣው ጨረታ ውስጥ ብር100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ በላይ ዋጋ በማቅረብ በጨረታው የሚሳተፍ ማንኛውም የአገር ውስጥ ተጫራች የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ወረቀት ኮፒ ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
  5. ጨረታ ሰነዱን በስራ ሰዓት ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት ፑል የአስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 705 ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
  6. ጨረታው በአንድ ኢንቨሎፕ የሚቀርብ ሆኖ ኦርጅናል ዶክመንት እና ኮፒ በታሸገ ኢንቨሎፕ ፖስታ በማጠቃለል ኮ/ቀ/ክ/ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 705 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርበታል።
  7. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከሎት 50,000 /ሀምሳ ሺ ብር ብቻ/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ብቻ በኮ/ቀ/ከ/ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት በሚል በማዘጋጀት ማስያዝ ይኖርባቸዋል ።
  8. ተጫራቾች በስራ ኢንተርፕራይዝ እና እንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት የተደራጁ ከሆነ ከተደራጁበት ተቋም የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ አለባችሁ።
  9. ጨረታው ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚያው ቀን ጠዋት 4፡30 የሚከፈት ሲሆን ነገርግን ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
  10. ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበው ጨረታ ሰነድ ስርዝ ድልዝ ኖሮት ካልተፈረመ፣ ፍሉድ ተጠቅሞ በጉልህ የማይነበብ ከሆነ ከውድድር ወጪ ይሆናሉ።
  11. መ/ቤቱ ከአሸናፊው ተጫራች ውል ከመፈረሙ በፊት በአሸናፊ ተጫራች አቅርቦት መጠን ላይ የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር እስከ 20% መጨመር ወይም መቀነስ የሚችል ይሆናል።
  12. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ ሆነው የተገኙባቸውን አገልግሎቶች ከአጠቃላይ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ የውል ስምምነት መፈፀም ይኖርባቸዋል።
  13. የጨረታውን አካሄድ ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጪ እንደሚሆኑ ፤ለወደፊትም በመንግስት ግዥ እንዳይሳተፉ እና ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና እንደሚወረስ ማወቅ አለባቸው።
  14.  መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።

አድራሻችን፡- ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ህንጻ 7ኛ ፎቅ ቢ/ቁ 705

አድራሻ፡- ቤቴል አደባባይ ወረድ ብሎ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አጠገብ

ስልክ ቁጥር 0118340591

የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ፑል

አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-30
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-30 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: ኮ/ቀ/ክ/ከተማ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት
  • Bid bond: 50,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published: Jun 18, 2026
  • Posted at: 2026-06-18T11:14:16.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders