Office and commercial space rental

የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/መምሪያ ካፌዎችንና ሱቆችን ለማከራየት ስለተፈለገ በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢ ድርጅቾች ማህበራት ግለሰብ መካከል በጨረታ አወዳድሮ ግዥውን ለመፈጸም ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/መምሪያ የሀዋሳ ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ በኮሪዶር ልማት የተገነቡ ካፌዎችንና ሱቆችን ለማከራየት ስለተፈለገ በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢ ድርጅቾች ማህበራት ግለሰብ መካከል በጨረታ አወዳድሮ ግዥውን ለመፈጸም ይፈልጋል።

በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ፡-

  1. በሥራ መስኩ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፤
  3. የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 ( ) በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 /ለአሥር ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ቀርባችሁ ለሰነድ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ወስዶ ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲ ፒ ኦ (CPO ) ወይም ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት።
  5. ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቬሎፕ አንድ ፋይናንሻል ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10(አሥር) ተከታታይ ቀናት በፋይ/ኢኮ/ልማ⁄ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዢ ኬዝ ቲም ) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. ጨረታው በ11ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከቀኑ 4.30 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል።
  7. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ ወይም በበዓላት ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል። የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
  8. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር 046-220-9963/ 046-212-1334

የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/መምሪያ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-29
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-29 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: Sidama
  • Publishing entity: Hawassa City Administration Finance & Economic Development Bureau
  • Bid bond: 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 500 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Jun 19, 2026)
  • Posted at: 2026-06-19T07:34:26.000Z
← Back to all tenders