ራከሮብ ቢዝነስ ኃ.የተ.የግል ማህበር በኤሌክትሮሜካኒካል፣ በኤሌክትሪካል፤ ሶላር ፓወር፤ በኬሚካል፣ ኮንስትራክሽን ማሺነሪዎችና መለዋወጫ ዕቃዎች እንዲሁም ተዛማጅ በሆኑ የንግድ ሥራ ዘርፍ ብቻ ላይ ለሚሰማሩ ተጫራቾች ሱቆቹን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል
Description
በድጋሚ የወጣ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር: (Rebid) RAC/01/2018
ራከሮብ ቢዝነስ ኃ. የተ. የግል ማህበር በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ጎርጎርዮስ አደባባይ አጠገብ በገነባቸው ሱቆች ውስጥ በኤሌክትሮሜካኒካል፣ በኤሌክትሪካል፤ ሶላር ፓወር፤ በኬሚካል፣ ኮንስትራክሽን ማሺነሪዎችና መለዋወጫ ዕቃዎች እንዲሁም ተዛማጅ በሆኑ የንግድ ሥራ ዘርፍ ብቻ ላይ ለሚሰማሩ ተጫራቾች ሱቆቹን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።
በዚህም መሠረት ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- ተጫራቾች ሊከራዩ በመረጡት ሱቅ በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ VAT Registration Certificate፤ እና የቲን ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 03 ጎርጎሪዮስ አደበባይ አጠገብ የኦሮሚያ ባንክ ከሚገኝበት ህንጻ 2ኛ ፎቅ በመቅረብ ውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚጫረቱባቸው ሱቆች ለየብቻ የአንድ ወር የኪራይ ዋጋ ቫትን ጨምሮ አሥር በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በራክሮብ ቢዝነስ ኃ. የተ. የግል ማህበር ስም አሰርተው ድርጅቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በታሸገ ፖስታ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ሱቆች የዋጋ ማቅረቢያ (Financial) ሠነድ ኦሪጂናል እና አንድ ኮፒ ለየብቻ ተለይቶ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ሰኔ 25 ቀን 2018 ከላይ በተራ ቁጥር 2 በተጠቀሰው አድራሻ ቢሮ ቁጥር 1263/201 በመምጣት ድርጅቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- ይህ ጨረታ ሰኔ 25 ቀን 2018 ልክ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት የተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
- የጨረታ አሸናፊዎች ማሸነፋቸው በጽሁፍ የሚገለጽላቸው እና የውል ስምምነት የሚፈፅሙ ይሆናል።
- በጨረታ ያላሸነፉ ድርጅቶች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፤
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ወሎ ሰፈር ጎርጎርዮስ አደባባይ አጠገብ የኦሮሚያ ባንክ በሚገኝበት ህንጻ 2ኛ ፎቅ፣
ስልክ ቁጥር 09 40 41 41 41፣ 09 40 42 42 42፣ 09 87 43 43 43
ራክርብ ቢዝነስ ኃ. የተ. የግል ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-07-02
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-07-02 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: ራክሮብ ቢዝነስ ኃ. የተ. የግል ማኅበር
- Bid bond: ለሚጫረቱባቸው ሱቆች ለየብቻ የአንድ ወር የኪራይ ዋጋ ቫትን ጨምሮ አሥር በመቶ (10%)
- Published: Jun 19, 2026
- Posted at: 2026-06-19T07:41:00.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.