የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት እየሩሳሌም መስፍን እና የፍ/ባለዕዳ እነ ዘውዴ ሃይለጊዮርጊስ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/271611 የካቲት 30 ቀን 2018 ዓ.ም እና በኮ/መ/ቁ/277261 በ24/07/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 05 የቤት ቁጥር 347 በቁጥር አ/03/29/16/23 በሴሪያል ቁጥር 001786 የተመዘገበ የቦታ ስፋት በካርታቸው መሰረት 554ካ/ሜ ሲሆን ቤቱ ያረፈበት 101ካ/ሜ ቤቱ በምስራቅ የቀበሌ (የመንግስት ቤት)፣ በምዕራብ የቀበሌ (የመንግስት ቤት)፣በደቡብ የቀበሌ (የመንግስት ቤት)፣ በሰሜን የውስጥ ለውስጥ መንገድ የሚያዋስኑት ሲሆን ከግቢው ለቤቱ የሚደርሰው በፕሮፖርሽን 30 ካ/ሜ ሲሆን በጠቅላላ በፕሮፖርሽን ለግለሰቡ የሚደርሰው የቦታ ስፋት 131 ካ/ሜ ቤቱ ከ2008ዓ.ም የተጀመረ የገዳም ሰፈር የመልሶ ማልማት ፕሮጀክት ስራ ክልል ውስጥ የሚገኝ ሲሆን በካሳ መመሪያ መሰረት ባላቸው ይዞታ እና በምርጫቸው መሰረት ምትክ ቦታ የሚመደብ እና በወቅታዊ የግንባታ ካሳ ክፍያ መሰረት የሚፈጸም ሆኖ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 6,524,063 (ስድስት ሚሊዮን አምስት መቶ ሃያ አራት ሺህ ስልሳ ሶስት) ሆኖ የትራንዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሐምሌ 13 ቀን 2018ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 4፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን። ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-20
  • Bid closing time: 10:30
  • Bid opening: 2026-07-20 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
  • Bid bond: 25%
  • Published: Jun 19, 2026
  • Posted at: 2026-06-19T07:46:09.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders