በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ማረሚያ ቤቶች አስ/ር ኮሚሽን የስልጤ ዞን የወራቤ ማረሚያ ተቋም በ2019 በጀት ዓመት በህግ ጥላ ስር ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች ለምግብ አገልግሎት የሚሆን ግብዓቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 01/2019

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ማረሚያ ቤቶች አስ/ር ኮሚሽን የስልጤ ዞን የወራቤ ማረሚያ ተቋም በ2019 በጀት ዓመት በህግ ጥላ ስር ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች ለምግብ አገልግሎት የሚሆን፡-

  • በሎት 1 ቅጭቅጭ የወጣለት የተበጠረ ሰርገኛ ጤፍ፣ በቆሎ፣ አተር፣ ፍርኖ ዱቄት፣ ባቄላ
  • በሎት 2 አንበሳ ሻይ ቅጠል፣ ጨው፣ ስኳር፣ ዘይት
  • በሎት 3 ጎመን ዘር፣ የተፈጨ በርበሬ፣ ቀይ ሽንኩርት፣ ነጭ ሽንኩርት፣ ሞኮረኒ፣ ፓስታ፣ ሩዝ፣ ምስር ክክ፣ አተር ክክ እና የተለያዩ ቅመማ ቅመም
  • በሎት 4 የማገዶ የባህር ዛፍ እንጨት ከሐምሌ 1/11/2018 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 30/4/2019 ዓ.ም በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህም መሠረት፡-

1. በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመደቡ

2. የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉና የንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ

3. ቫት /VAT/ ተመዝጋቢ የሆነ

4. ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ለ60 ቀናት

5. አሸናፊው ማንኛውንም ወጪ በራሱ ሸፍኖ ዕቃዎችን ወራቤ ማረሚያ ተቋም ቅጥር ግቢ ማቅረብ የሚችል

6. የጨረታው ማስከበሪያ 5000 (አምስት ሺህ ብር) በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ እውቅና ያለው የፋይናንስ ተቋም የተረጋገጠ ቼክ፣ ሌተር ኦፍ ክሬዲት፣ ሲፒኦ ማቅረብ የሚችሉ

7. በጨረታው አሸናፊ የሚሆኑ ታጫራቾች በአሸነፉባቸው ዕቃ አይነቶች 10% ማስያዝ የሚችል

8. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ለሚወዳደሩበት አቅርቦት በዘርፉ የማይመለስ ብር 150 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከግዥና ፋይናንስ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ

9. ታጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውንና የመወዳደሪያ ሂሳባቸውን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ አንድ ኦርጅናል እና አንድ ፎቶ ኮፒ እስከ 15ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

10. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ11፡00 ሰዓት ታሽጎ በ16ኛው ቀን በ3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

11. ተቋሙ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 09 11 80 41 23 መጠየቅ ይችላሉ።

የወራቤ ማረሚያ ተቋም


Tender details

  • Deadline: 2026-07-03
  • Publishing entity: Werabe Correctional Institute
  • Bid bond: 5,000.00 ብር
  • Bid document price: 150.00 ብር
  • Published: Jun 19, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders