የኢትዮዽያ አየር መንገድ ጡረተኞች ሁለገብ የኮንትራት ሥራዎች ኃላ/የተ/ኅ/ሥ/ማህበር በሥሩ ለሚገኙ ሁለት ካፍቴሪያዎች ተቆራጭ ኬክ፣ ብስኩት፣ ሳምቡሳ (የምስር)፣ የወተት ተዋፅኦ፣ እንቁላል፣ የተዘጋጁ የዶሮ ብልቶች፣ ለስላሳ መጠጦች (በፕላስቲክ የታሸጉ) የማዕድን ውሃዎች በግማሽ በአንድ እና በሁለት ሊትር መጠን ያላቸው በጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ጋር ውል በመዋዋል የዱቤ ግዢ መፈጸም ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮዽያ አየር መንገድ ጡረተኞች ሁለገብ የኮንትራት ሥራዎች ኃላ/የተ/ኅ/ሥ/ማህበር በሥሩ ለሚገኙ ሁለት ካፍቴሪያዎች የሚከተሉትን በጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ጋር ውል በመዋዋል የዱቤ ግዢ መፈጸም ይፈልጋል።

1. ተቆራጭ ኬክ ፤ብስኩት ፣ ሳምቡሳ (የምስር )፤

2. የወተት ተዋፅኦ ፤ እንቁላል ፤ የተዘጋጁ የዶሮ ብልቶች፣

3. ለስላሳ መጠጦች (በፕላስቲክ የታሸጉ) የማዕድን ውሃዎች በግማሽ በአንድ እና በሁለት ሊትር መጠን ያላቸው፤

ስለዚህ ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ የንግድ ድርጅቶች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።

1. የዘመኑ ግብር የተከፈለበት የንግድ ፈቃድ ያለው ያላት።

2. ተጫራቾች የመጫረቻውን ቅጽ (ፎርም) ብር 200.00 በመክፈል ከማህበሩ ጽ/ቤት ቢሮ ማግኘት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት አይነት የሚሸጡበትን ዋጋ በጨረታው ቅጽ (ፎርም) ላይ በትክክል ሞልተው የድርጅታቸውን ሕጋዊ ማህተም በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ሰኔ 22 ቀን ከቀኑ 6:00 ሰዓት ድረስ በማህበሩ ጽ/ቤት ቢሮ ማስገባት አለባቸው።

4. ጨረታው ሰኔ 22 ቀን በ8:30 ሰዓት በማህበሩ ጽ/ቤት ቢሮ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

5. ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው በደብዳቤ, ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ ባሉት 5 የስራ ቀናት ውስጥ ማህበሩ ጽ/ቤት ቀርበው ውል መፈራረም አለባቸው።

6. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡-

  • የስልክ ቁጥር- 0911-17-51-49 /0115-17-82-83 ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጠዋቱ 2:00-1፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ደውለው መረዳት ይችላላሉ ።
  • የማህበሩ ጽ/ቤት በኢትዮዽያ አየር መንገድ ግቢ ውስጥ የሠራተኞችና የመንገደኞችማጓጓዣ አውቶብሶችና እና ላንድ ክሩዘሮች ከሚቆሙበት መናኻሪያ ከስምሪት ቢሮ አጠገብ ይገኛል።

የኢትዮዽያ አየር መንገድ ጡረተኞች ሁለገብ የኮንትራት ሥራዎች ኃላ/የተ/ኅ/ሥ/ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-06-29
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid opening: 2026-06-29 14:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: የኢ.አ.መ. ጡረተኞች የኮንትራት ሥራዎች ኃላ/የተ/ኅ/ሥራ ማኅበር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: Jun 21, 2026
  • Posted at: 2026-06-22T08:46:37.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders