የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ያገለገሉ ጎማዎች፣ ያገለገሉ የመኪና መለዋወጫዎች እና ሌሎችም ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የመጣ ያገለገሉ ዕቃዎች

ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት እንቁላል ፋብሪካ አካባቢ በሚገኘው ዋና መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ እና መጋዘን እንዲሁም በሜክሲኮ አካባቢ በሚገኝ መጋዘን ውስጥ የሚገኙትን የተለያዩ ዕቃዎች

  • (የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ 
  • ያገለገሉ ጎማዎች፣
  • ያገለገሉ የመኪና መለዋወጫዎች እና
  • ሌሎችም ዕቃዎች) ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ባወጣው የዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች፡-

  1. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የሽያጭ ጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል እንቁላል ፋብሪካ አካባቢ በሚገኘው የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት መ/ቤት ቅጥር ግቢ የፋይናንስ ቢሮ በመገኘት እና ክፍያ በመፈጸም ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ከሰኔ 15/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 25/2018 ዓ.ም ከቀኑ 6:30 ሰዓት ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይቻላል።
  2. በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚያቀርቡትን አጠቃላይ ዋጋ 2% ለስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት /Refugees and Returnees Service / በሚል የተዘጋጀ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ የባንክ ዋስትና /Bank Guarantee/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  3. ማንኛውም ተጫራች ከሰኔ 15/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 25/2018 ዓ.ም ድረስ ባሉት የስራ ቀናት  ዘወትር በስራ ሰዓት ጉለሌ በሚገኘው የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ በመገኘት ዕቃዎቹን መመልከት ይችላል። ቅዳሜና እሁድ የስራ ቀናት አይደሉም።
  4. ጨረታው ጉለሌ እንቁላል ፋብሪካ በሚገኘው የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ የሚካሄድ ሲሆን የጨረታው ሳጥን ሰኔ 25/2018 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ታሽጎ በዕለቱ ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል።
  5. የጨረታ አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ያስያዙት ሲፒኦ ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ዋሰትና በ3 ቀናት ውሰጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
  6. ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን መረከብ አለባቸው።
  7. በተራ ቁጥር 6 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ ተጨራች ለጨረታው ማስከበርያ ያስያዘው ሲፒኦ ለአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ገቢ በማድረግ የተሻለውን አማራጭ የመውሰድ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  8. አገልግሎት መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  9. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 91 047 4668 ወይም 251 91 156 9913 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-02
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-07-02 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Refugee and Returnee Service
  • Buyer address: ከዋሽንግተን የህክምና ማዕከል 500 ሜትር ያህል ገባ ብሎ ወደ ቦሌ ሚካኤል በሚወስደው መንገድ ላይ
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: Jun 21, 2026
  • Posted at: 2026-06-22T09:39:28.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders