ፀደይ ባንክ /አ.ማ/ ደ/ማርቆስ ዲስትሪክት ስፋቱ 150 ካ.ሜ የሆነ የመኖሪያ ቤትና ቦታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ፀደይ ባንክ/አ.ማ/ ደ/ማርቆስ ዲስትሪክት

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሀራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

ጸደይ ባንክ አ.ማ ለወ/ሮ መሰረት ተሻገር ለሰጠው ብድር በዋስትና ያስያዘውን በደ/ማርቆስ ከተማ በካርታ ቁጥር K/አብ-01007 የተመዘገበ በአዋሳኝ በምስራቅ መንገድ፣ በምዕራብ ያሳብ አያሌው፣ በሰሜን ዳዊት አያሌው፣ በደቡብ ሽበሽ ገላየ የሚያዋስነው ስፋቱ 150 ካ/ሜ የሆነ የመኖሪያ ቤትና ቦታ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በድጋሚ ለ2ኛ ጊዜ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

  1. ተጫራቾች የቤቱን የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4ኛ በጥሬ ገንዘብ ወይም ሲፒኦ በጸደይ ባንክ ስም ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
  2. የቤቱ ጨረታ መነሻ ዋጋው ብር 3,452,861,48 /ሶስት ሚሊዮን አራት መቶ አምሳ ሁለት ሺ ስምንት መቶ ስልሳ አንድ ከአርባ ስምንት ሳንቲም/ ነው።
  3. በጨረታ የሚሳተፈው በህግ ሰውነት ያገኘ ድርጅት ከሆነ የድርጅቱን የጸደቀ የመመስረቻ ጽሁፍ እና መተዳደሪያ ደንብ፣ ህጋዊ ሰውነት ያገኘበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ህጋዊ ውክልና ማቅረብ አለበት።
  4. የጨረታ አሸናፊው አሸናፊነቱ የሚረጋገጠው የጨረታው ውጤት በሚመለከተው አካል ጸድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠው ይሆናል።
  5. የጨረታ አሸናፊው ያሸነፈበትን ቀሪውን ገንዘብ በ15 ቀን ውስጥ ለባንኩ በመክፈል ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል:: በዚህ ቀን ውስጥ ካልከፈለ ግን ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው 1/4ኛ ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።
  6. በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል።
  7. የጨረታ አሸናፊው ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያየዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጭዎችን ይከፍላሉ:: ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ለቀሪው የሊዝ ክፍያ ገዥው ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል።
  8.  ተጫራቾች ቤቱን በባንኩ አማካኝነት መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ።
  9. ጨረታው የሚካሄደው ደ/ማርቆስ ከተማ ቀበሌ 13 ለጨረታ በወጣው ንብረት ውስጥ ነው።
  10. ጨረታው የሚካሄደው ሃምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ 6፡30 ሰዓት ይሆናል።
  11. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0912436868 / 0921667115 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።


Tender details

  • Deadline: 2026-07-27
  • Bid closing time: 12:30
  • Bid opening: 2026-07-27 12:30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Tsedey Bank S.C. Debre Markos District
  • Bid bond: 25%
  • Published: Jun 21, 2026
  • Posted at: 2026-06-22T09:59:46.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders