ሕብረት ባንክ አ.ማ. በቅርንጫፎቹ በኩል ለሰጣቸው ብድሮች በመያዣነት የያዛቸውን ንብረቶች በግልፅ ሐራጅ (ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል

Description

የሐራጅ ማስታወቂያ

ሕብረት ባንክ አ.ማ. በቅርንጫፎቹ በኩል ለሰጣቸው ብድሮች በመያዣነት የያዛቸውንና ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልፅ ሐራጅ (ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል።

.

የተበዳሪ ስም

የአስያዥ ስም

አበዳሪው ቅርንጫፍ

ንብረቶቹ የሚገኙበት አድራሻና የቦታ ስፋት

የይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ቁጥር

የሐራጅ መነሻ ዋጋ በብር

ሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት

1

ጌደብ ጠቅላላ ንግድ /የተ/ የግ/ማህበር

ጌደብ ጠቅላላ ንግድ /የተ/ የግ/ማህበር

በሻሌ

ሽገር ከተማ፣ ሱሉልታ /ከተማ፣ የቦታ ስፋት 5,000 . የሆነ መጋዘን፤

EMMLM/ SUL/7/2006

30,061,010.88

ሐምሌ 16 ቀን 2018 . 5:00 እስከ 6:00 ሰዓት

2

አቶ ንጋቱ ኤሊያስ

አቶ ንጋቱ ኤሊያስ

አለታ ጩኮ

ሀዋሳ ከተማ፣ ቱላ /ከተማ፣ ቀበሌ ዳቶ፣ የቦታ ስፋት 105 . ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውል ቤት

8688

3,003,842.96

ሐምሌ 16 ቀን 2018 . ከቀኑ 500 እስከ 600 ሰዓት

3

/ መስከረም ፍቃዱ በረዳ

/ ንጋቷ ተፈራ፣ / መስከረም ፈቃዱ፣ / ብዙነሽ ፈቃዱ፣ / አመለወርቅ ፈቃዱ፣ አቶ በላይ ፈቃዱ እና / ሸዋዬ ፈቃዱ

ጅማ

ጅማ ከተማ፣ አወቱ መንደራ ቀበሌ፣ የቦታ ስፋት 1,049.32 . አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ ቤት

21031062 (OR004050 507006)

5,799,422.66

ሐምሌ 16 ቀን 2018 . ጡዋት 500 እስከ 600 ሰዓት

4

አቶ ኡዋር ኦፒየው ኦዶላ

አቶ ማክረ አጋሃ

ጋምቤላ

ጋምቤላ ከተማ ቀበሌ 04 የቦታ ስፋት 920 . አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ ቤት፤

30213/07

5,903,838.89

ሐምሌ 21 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 500 እስከ 600 ሰዓት

የሐራጅ ደንቦች፡-

1. ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በሕብረት ባንክ አ.ማ.(Hibret Bank S.C) ስም የተሰራ የባንክ ክፍያ ማዘዣ(ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ። ከባንክ ክፍያ ማዘዣ(ሲ.ፒ.ኦ) ውጭ የሚቀርብ የጨረታ ማስያዣ ተቀባይነት የለውም።

2. ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከቅርንጫፎቹ ወይም ከብድር ማስመለስ እና ፎርክሎዠር ዋና ክፍል ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ዕለት ሶስት ቀናት በፊት መጎብኘት ይችላል።

3. በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪ እና አስያዥ ብቻ ናቸው። ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል። ተጫራቾች የሕግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ደግሞ ሕጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሐራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ሰው ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ፅ/ቤት ወይም በተመሳሳይ አካል የፀደቀ መመስረቻ ፅሁፍ(የመተዳደሪያ ደንብ)፣ ቃለ ጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ መቅረብ አለበት።

4. የተጠቀሱት ንብረቶች ሐራጅ የሚካሄደው ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ላይ ነው።

5. የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይደረጋል።

6. ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል። ከፍተኛ ዋጋ ለሰጠ ተጫራች ደግሞ ያቀረበውን ዋጋ ባንኩ ሲቀበለው ያሽነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ እንዲከፍል የሚገልፅ ደብዳቤ የሚሰጠው ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል። በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል።

7. ከፍ ሲል የተጠቀሱትን ንብረቶች ለሚገዛና የባንኩን የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መመዘኛዎች ለሚያሟላ ተጫራች በሚሰጠው ከፍተኛ ዋጋ ላይ ባንኩ እስከ 50%(ሃምሳ በመቶ) ብድር ሊያመቻች ይችላል።

8. የጨረታው አሸናፊ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች የጨረታ አሸናፊ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን ይከፍላል።

9. ባንኩ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10. ለተጨማሪ መረጃ በአበዳሪ ቅርንጫፍ ቢሮዎች በአካል እንዲሁም በዋናው መ/ቤት በስልክ ቁጥር 011 470 6380 / 011 466 6593 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።


Tender details

  • Deadline: 2026-07-28
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-07-28 12:00
  • Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Hibret Bank S.C.
  • Bid bond: 25%
  • Published: Jun 21, 2026
  • Posted at: 2026-06-22T11:00:35.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders