አቢሲንያ ባንክ አ.ማ. መኖሪያ ቤት ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ሐራጅ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውንና በሠንጠረዡ የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ንብረቱ ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

  • ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋውን ¼  (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው ለመሳተፍ ይችላሉ።
  • የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል። በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።
  • በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል።
  • ተበዳሪው/መያዣ ሰጪው በሐራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ። ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።
  • የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን፣ ግብር በተጠቀሱት ንብረቶች ላይ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጪዎች ገዢ ይከፍላል። ውዝፍ የሊዝ ዕዳ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ቀሪ የወደፊት የሊዝ ክፍያ ዕዳ ወደ አሸናፊው /ገዢ/ የሚተላለፍ ይሆናል።
  • ንብረቱን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አሲዞ ለመጎብኘት ወይም ለማየት ይቻላል።
  • በባንኩ ብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟሉ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢዎች ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል።
  • የጨረታው ቦታ አ.አ አቢሲኒያ ባንክ ዋና መስሪያቤት 4ኛ ፎቅ ለጨረታ በተዘጋጀ ክፍል ውስጥ ነው።
  • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 01 200 7038 እና 011 554 6737 አ.አ በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
  • ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተ.ቁ

የተበዳሪው ስም

የመያዣው ሰጪው ስም

የንብረቱ ዓይነትና አገልግሎት

የቦታው ስፋት

 

የባለቤት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር

ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ

የጨረታ መነሻ ዋጋ

ጨረታው የሚካሄድበት ቀን 

የምዝገባ ሰዓት

የጨረታ ሰዓት

1

ቢዘዋን ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

አቶ ኑሩ ሸፈቀ

መኖሪያ ቤት

 

200 ካ.ሜ

 

BRU/4380/2000

 

ሸገር ከተማ ቡራዩ ክ/ከተማ

3,850,541.38

 

ሀምሌ 15 ቀን 2018 ዓ.ም

4:30-5:30

 

5:30-6:00

 

 


Tender details

  • Deadline: 2026-07-22
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid opening: 2026-07-22 12:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Bank of Abyssinia S.C.
  • Buyer address: Addis Ababa Ethiopia
  • Bid bond: 25%
  • Published: Jun 21, 2026
  • Posted at: 2026-06-22T11:33:15.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders