ብርሃን ባንክ አ.ማ. ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የሐራጅ ማስታወቂያ
ብርሃን ባንክ አ.ማ ከባለእዳዎቹ ላይ ሚፈልገው ገንዘብ በዋስትና የያዛቸውን እና ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/1990 እና በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 216/92 ለባንኮች በተሰጠው ስልጣን መሠረት ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች በመገንዘብ ማክበር ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋውን የ1/4 (አንድ አራተኛ) (ሲፒኦ) በብርሃን ባንክ አማ ስም ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን እንዳሸነፈ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ ንብረቱን መረከብ አለበት። በእነዚህ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል። በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ይመለስላቸዋል።
- የመኖሪያ ንግድ ቤቶቹ ጨረታ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ይከናወናል።
- የጨረታ አሸናፊው በሚገዛው ንብረት ላይ የሚፈለግ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ግብር፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የስም ማዛወሪያ ክፍያዎች እና የሊዝ ክፍያዎች ይመለከተዋል።
- መያዣ ሰጪዎች ሐራጁ በሚከናወንበት ቦታ ቀንና ሰዓት መገኘት ይችላሉ። ባይገኙ ግን ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።
- በባንኩ ብድር መምሪያ መስፈርት መሰረት እና በተሰጠው ጊዜ ውስጥ የሚፈለግበትን ለሚያሟላ ተጫራች ባንኩ በከፊል ብድር ሊያመቻች ይችላል።
- ለጨረታ የቀረቡትን ንብረቶች በስራ ስዓት ኘሮግራም አስይዞ ለመጐብኘት ይቻላል።
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው።
የመኖሪያ እና ንግድ ቤቶች
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪዉ ስም |
የመያዣ ሰጭዉ ስም |
መኖሪያ/ የንግድ ቤት የሚገኝበት አድራሻ |
የቦታው ስፋት በካሬ ሜትር |
የንብረቱ አገልግሎት |
የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር |
የጨረታ መነሻ ዋጋ |
ጨረታዉ የሚካሄድበት ቀን እና ሰዓት፤ |
|
1 |
ሌንጮ አብዱልሃቅ |
ሌንጮ አብዱልሃቅ |
አዳማ ከተማ ቦኩ ሸነን ቀበሌ |
105.2 ካ.ሜ
|
መኖሪያ ቤት |
OR0011 76105008 |
2,700,000.00
|
ሐምሌ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-5፡30 |
|
2 |
ኤስ ኬ ኮንስትራክሽን |
አምሐ ኃይሉ |
አ/አ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 04 |
57.76 ካ.ሜ
|
ንግድ
|
AA000070 405637231
|
3,600,000.00
|
ሐምሌ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-5፡30 |
|
3 |
መቅደስ ቦጋለ |
መቅደስ ቦጋለ |
ሸገር ከተማ ኮዬ ፈጬ ክ/ ከተማ ኮዬ ፈጬ ሳይት ኮንዶሚኒየም(B-520) |
41.96 ካ.ሜ
|
መኖሪያ ቤት |
OR0000709 022925200004
|
1,950,000.00 |
ሐምሌ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-5፡30 |
|
4 |
እመቤት ጌታቸዉ |
እመቤት ጌታቸዉ |
ሰንዳፋ በኬ ከተማ 02 ቀበሌ |
200 ካ.ሜ
|
መኖሪያ ቤት |
470/1740/99 |
2,500,000.00
|
ሐምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-5፡30 |
|
5 |
ታሪኩ ዶሌ |
ታሪኩ ዶሌ |
ሆሳዕና ከተማ አዲስ ከተማ ክ/ከተማ አምባ ማዕከል ቀበሌ |
587 ካ.ሜ
|
ንግድ
|
CLB/100/06 |
45,743,415.00
|
ሐምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-5፡30 |
ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች 011-650 6900 እና 011-650 6276 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
Tender details
- Deadline: 2026-07-24
- Bid closing time: 11:30
- Bid closing (note): የሐራጁ መዝጊያ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-07-24 11:30
- Bid opening (note): የሐራጁ መክፈቻ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Berhan Bank S.C.
- Bid bond: 25%
- Published: Jun 21, 2026
- Posted at: 2026-06-22T11:36:34.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.