አቢሲንያ ባንክ አ.ማ. የመኖሪያ ቤት ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውንና በሠንጠረዡ የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ የቀረበዉን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል። በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል። በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ወዲያዉ ይመለስላቸዋል።
- ተበዳሪው /መያዣ ሰጪው/ በሐራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ። ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።
- የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል። ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ለቀሪው የሊዝ ክፍያ ገዢው ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል።
- ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ወይም ማየት ይቻላል።
- በባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟላ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ /አሸናፊ/ ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል።
- የጨረታው ቦታ አዲስ አበባ ከተማ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ለገሀር በሚገኘው የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 515 1153 እና 011 515 0711 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪው ስም |
የመያዣ ሰጪው ስም |
የንብረቱ አይነት እና አገልግሎት |
የቦታው ስፋት በካ.ሜ |
የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር |
ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ |
የጨረታው መነሻ ዋጋ በብር |
ጨረታው የሚካሄድበት ቀን |
የምዝገባ ሰዓት |
የጨረታ ሰዓት |
ጨረታው የወጣው |
|
1 |
አቶ ደመላሽ ታደሰ ዓሊ |
ተበዳሪዉ
|
የመኖሪያ ቤት
|
105 |
AA000090701126
|
አዲስ አበባ ከተማ ኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ ከተማ ወረዳ 07 |
6,741,507.79
|
ሐምሌ 15 ቀን 2018 ዓ.ም
|
8:30-9:30
|
9:30-10:00
|
በድጋሚ
|
|
2 |
አቶ ደመላሽ ታደሰ ዓሊ |
ወ/ሮ እታየሁ አስታጥቄ |
የመኖሪያ ቤት
|
105 |
AA000090701487
|
አዲስ አበባ ከተማ ኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ ከተማ ወረዳ 07 |
7,227,177.21
|
ሐምሌ 16 ቀን 2018 ዓ.ም
|
4:30-5:30
|
5:30-6:00
|
በድጋሚ |
|
3 |
ሁምኔሳ ሶሪ
|
ወ/ሮ ዳዊ ጫልቺሳ |
የመኖሪያ ቤት |
140 |
BUR/WIMT/2119/2013/200
|
ሸገር ከተማ ገፈርሳ ጉጄ ክ/ከተማ |
5,034,124.96
|
ሐምሌ 16 ቀን 2018 ዓ.ም |
8:30-9:30
|
9:30-10:00
|
በድጋሚ
|
Tender details
- Deadline: 2026-07-23
- Bid closing time: 16:00
- Bid closing (note): የሐራጁ መዝጊያ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-07-23 16:00
- Bid opening (note): የሐራጁ መክፈቻ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Bank of Abyssinia S.C.
- Buyer address: Addis Ababa Ethiopia
- Bid bond: 25%
- Published: Jun 21, 2026
- Posted at: 2026-06-22T11:39:27.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.