ዘመን ባንክ አ.ማ. ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውል ቤት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የሐራጅ ማስታወቂያ

ዘመን ባንክ አ.ማ ብድር ሲስጥ በመያዣነት የያዘውን ከዚህ በታች የተመለከተውን መኖሪያ ቤት ባለበት ሁኔታ በአዋጅ ቁጥር 97/1990 እንደተሻሻለው) በተሰጠው ስልጣን መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ተ.ቁ

የተበዳሪው ስም

የአስያዡ ስም

የንብረቱ አድራሻ

የቤት ቁጥር

የቦታው ስፋት በካሬ ሜ

የካርታ ቁጥር

 

የንብረቱ ዓይነት

 

የሐራጅ መነሻ ዋጋ

 

ሐራጅ የሚከናወንበት

የሐራጁ ደረጃ

 

ከተማ

ወረዳ

 

ቀን

 

የምዝገባ ሰዓት

የጨረታው ሰዓት

 

 

ዶ/ር ዮሐንስ ግርማ ዘውዴ እና ወ/ሮ ሐና የሺዋስ ገናጥሩነህ

ዶ/ር ዮሐንስ ግርማ ዘውዴ እና ወ/ሮ ሐና የሺዋስ ገናጥሩነህ

ሸገር ከተማ ገላን ክ/ከተማ

 

_

_

399 ካሬ ሜ.

 

23085802 ፓርሴል ኮድ OR030031217007

 

ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውል ቤት

 

ብር 9,321,481.95 (ዘጠኝ ሚሊዮን ሶስት መቶ ሃያ አንድ ሺህ አራት መቶ ሰማኒያ አንድ ብር ከ95/100)

ሐምሌ 15 ቀን 2018 ዓ.ም

ጠዋት 3:30-5:00

 

ጠዋት 5:00_ 5:50

 

በድጋሚ

 

 

የሐራጅ ደንቦች፡-

1. ተጫራቾች የንብረቱን የመነሻ ዋጋ 1/4 (አንድ አራተኛ) የጨረታ ማስከበሪያ በዘመን ባንክ አ.ማ ስም የተዘጋጀ በባንክ በተመሰከረ የክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።

2. አሸናፊው/ዋ የሚለየው በደብዳቤ ሲገለጽ ነው:: አሸናፊው/ዋ አሸናፊነታቸው በደብዳቤ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ አጠቃለው መክፈል አለባቸው:: ይህንን ካላደረጉ ያስያዙት ሲፒኦ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፣ እንደገና ጨረታው ይካሄዳል፣ የዋጋ መቀነስ ከተከሰተ አግባብነት ባላቸው ህጎች መሰረት ልዩነቱን የመጀመሪያው አሸናፊ እንዲከፍሉ ይጠየቃሉ።

3. ጨረታው በሚካሄድበት አዳራሽ ውስጥ መገኘት የሚችሉት ሲፒኦ ያስመዘገቡ ተጫራቾች ብቻ ናቸው።

4. ንብረቱን አስመልክቶ ማንኛውንም ለመንግስት ሊከፈል የሚገባውን ክፍያ የንብረት ግብር፣ የቤት ማህበር መዋጮ፣ ውዝፍ ሊዝ ክፍያ፣ የአከራይ ተከራይ ግብር፣ ያልተከፈሉ ክፍያዎች ወዘተ (ካሉ) እነዚህን ክፍያዎች በሙሉ በጨረታው አሸናፊ የሚከፈል ይሆናል።

5. የሐራጅ ሂደቱ ከተጀመረ በኃላ ማንም ተጫራች መውጣት እና መግባት አይፈቀድም፣ ተጫራቹ ሳይፈቀድለት ማናቸውንም ዓይነት ንግግር ማድረግ አይችልም:: ይህንን ደንብ የማያከብር እና ጨረታውን የሚያውክ ተጫራች ካለ እንዲወጣ ተደርጎ ጨረታው በቀሩት ተጫራቾች ይቀጥላል።

6. የባንኩን የብድር ፖሊሲ እና ሥነሥርአት ለሚያሟሉ ተጫራቾች የንብረቱን የሐራጅ መነሻ ዋጋውን መጠን በከፊል የሚሸፍን ብድር ባንኩ ሊያመቻች ይችላል:: ባንኩ ብድሩን በማናቸውም ሁኔታ ለአሸናፊው ባይፈቀድ/ባይሰጥ አሸናፊው በዚህ የሐራጅ ደንብ ተ.ቁ 2 ላይ የተቀመጠውን ግዴታ እና ሌሎች ግዴታዎችን አያስቀርላቸውም።

7. ባንኩ ንብረቱን በገዥው ስም እንዲዞር ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይፅፋል:: ከስም ዝውውር ጋር ያሉ ማናቸውንም ክፍያ ገዥው ይከፍላል።

8. የሐራጅ ሽያጩ የሚከናወነው ሰንጋ ተራ በሚገኘው በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 18ኛ ፎቅ ላይ ነው።

9. ባንኩ በሚያወጣው የጉብኝት ፕሮግራም መሰረት ተጫራቾች የሚሸጠውን ንብረት መጎብኘት ይችላሉ።

10. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-6-68 62 16 ወይም 0911152490 ወይም 0911456203 ወይም 0919 60 26 48 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

11. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ዘመን ባንክ አ.ማ

Sengatera, Ras. Abebe Aregay Street, P.O.Box 1212 Addis Ababa, Ethiopia


Tender details

  • Deadline: 2026-07-22
  • Bid closing time: 11:00
  • Bid opening: 2026-07-22 11:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Zemen Bank S.C.
  • Buyer TIN: 0004608547
  • Buyer address: Josef Tito Street
  • Bid bond: 25%
  • Published: Jun 21, 2026
  • Posted at: 2026-06-22T12:21:56.000Z
  • Buyer website: https://www.zemenbank.com

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders