የቦታው ስፋት 550 ካ.ሜ. የሆነ ቤት ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት ወ/ሮ ሊቨን ተፈሪ እና የፍ/ባለዕዳ እነ አቶ ሰለሞን ታደሰ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ/በኮ/መ/ቁ/208400 በ27/05/2008 ዓ/ም እና በ21/9/2009ዓ/ም በኮ/መ/ቁ/208400 በ27/05/2008 ዓ/ም የፌ//ጠቅላይ ፍ/ ቤት በ23/03/2012 ዓ/ም በመ/ቁጥር/146508 በመጋቢት 26 ቀን 2010 ዓ/ም የፌ/መ/ደ/ፍ/ በኮ/መ/ቁ/247665 በ27/11/2013 ዓ/ም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.247665 በቀን መጋቢት 17 ቀን 2018ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 9 የቤት ቁጥር አዲስ ሊዝ ቁጥር 0269 ሴርያል ቁጥር 0737 የቦታው ስፋት 550 ካ.ሜ. በሰነድ መብት የተፈጠረለት የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 46,362,506.70 (አርባ ስድስት ሚሊዮን ሶስት መቶ ስልሳ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ስድስት ከ70/100) ሆኖ የትራክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሐምሌ 16 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት፤ ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 11 273 0852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-07-23
- Bid closing time: 11:00
- Bid opening: 2026-07-23 11:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published: Jun 22, 2026
- Posted at: 2026-06-23T07:35:55.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.