በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ የውጊያ ቴክኒክ ትምህርት ቤት የተለያዩ አገልግሎቶችን መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር፡- ሙ/ቴ/ት/ቤት ግ/ጨ 001/2019
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ የውጊያ ቴክኒክ ትምህርት ቤት ባለው በጀት፡-
1ኛ. ለት/ቤቱ ሰራዊት አባላትና ሲቪል ሰራተኞች አውቶቢስ (ደረጃ) እና እንደ አስፈላጊነቱ ለፊልድና ሰርቪስ አገልግሎት በቀን 96 ኪሎ ሜትር የሚጓዝ በ5 የስራ ቀን እና ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ 7 ቀናት አገልግሎት የሚሰጥ፤
2ኛ.ለት/ቤቱ ከፍተኛ መኮንኖች ከመኖሪያ ሰፈር ወደ ቢሮ ከቢሮ ወደ ስልጠና ወረዳ እና እንደ አስፈላጊነቱ ለፊልድ ስራሃይሩፍ (ደረጃ 1) ሰርቪስ አገልግሎት በቀን 150 ኪሎ ሜትር የሚጓዝ በ5 የስራ ቀን እና ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ 7 ቀናት አገልግሎት የሚሰጥ በጨረታ ሰነዱ ክፍል 6 ላይ በተገለፀው መሰረት፣
3ኛ.የቤትና ቢሮ መገልገያ ዕቃዎች የአገልግሎት ግዥ የፎቶ ኮፒማሸን፣ በኤሌክትሪክ የሚሰራ ስቶቭ፣የኤሌክትሪክ ምድጃ፣ የቁምና አግድም ፍሪጅ፣ ኤርኮንዲሽነር፣ ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተር፣ ላፕቶፕ ኮምፒወተር፣ ፕሪንተር፣ ወዘተ... የቤትና የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች
በጨረታ ሰነዱ ክፍል 6 ላይ በተዘረዘሩት የብልሽት ሁኔታዎች በጨረታ በማወዳደር የአንድ ዕቃ ዋጋ፣ ሰርቪስ ለማድረግ የእጅ ዋጋ እና ለመጠገን የእጅ ዋጋ መነሻ በማድረግ መለዋወጫዎችን ማቅረብ መጠገን የሚችሉ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅት ጋር እስከ ሰኔ 30/2019 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ የውል ስምምነት በመፈፀም በየጊዜው ማስጠገን፣
4ኛ.የሆቴል የመስተንግዶ አገልግሎት ግዥ ለሀገር ውስጥ ከፍተኛ መኮንኖችን እና ከውጭ ሀገር ለስራና ለጉብኝት ለሚመጡ እንግዶች በጨረታ ሰነዱ ክፍል 6 ላይ የተገለፀው በአከባቢያችን ከሚገኝ የሆቴል አገልግሎት ግዥ ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ከአሸናፊው ጋር እስከ ሰኔ 30/2019 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ የውል ስምምነት በመፈፀም አገልግሎቱን ማግኘት፡-
በጨረታ ሰነዱ ክፍል 6 ላይ በተገለፁት መሠረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ማናቸውም ተጫራቾች፡ በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ፣የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የአቅራቢነት የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ስለ ግብር አከፋፈል የሚሰጥ ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ፣ ተያያዥነት ያላቸው ማስረጃዎች ለአውቶቢስ ሰርቪስ አገልግሎት በተጨማሪ ለሃይሩፍ ሰርቪስ አገልግሎት ሙሉ ኢንሹራንስና የ3ኛ ወገን ኢንሹራንስ ኮፒ፣ የመድን ዋስትና፣የመንገድ ፈንድ፣ ቦሎ እና የተሽከርካሪዎችን የቴክኒክ ፍተሻ ብቃት ማረጋገጫ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የተሟሉ በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጁ የጨረታ ሰነዶችን ከዚህ በታች በቁጥር 6/ሐ/ በተገለፀው አድራሻ ማግኘት ይችላሉ። በቁጥር 6 “ለ” በተገለፀው አድራሻ የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ሰኔ 15/2018 ዓ.ም ጀምሮ በተከታታይ 10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ የመጫረቻ ሰነዳቸውን ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
በተጨማሪም በጨረታ ሰነዱ ክፍል 6 ላይ በሒሳብ መደብ 6252 (የአውቶቢስ ሰርቪስ አገልግሎት) የሚካፈሉ ተጫራቾች ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)፤ በሒሳብ መደብ 6252 (ለሃይሩፍ ሰርቪስ አገልግሎት) የሚካፈሉ ተጫራቾች ብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) ለጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ከታወቀ ባንክ ሲፒኦ (CPO) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። በሒሳብ መደብ 6233 (ለሆቴል መስተንግዶ አገልግሎት) የሚካፈሉ ተጫራቾች ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ለጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ከታወቀ ባንክ ሲፒኦ (CPO) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። በሒሳብ መደብ 6243 የሚካፈሉ ተጫራቾች ብር 10.000.00 (አስር ሺህ ብር) ለጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ከታወቀ ባንክ ሲፒኦ (CPO) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቁጥር 6 “መ” በተገለፀው አድራሻ የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ (ተከታታይ ቀናት ተቆጥረው) በ10ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ይከፈታል። ሁሉም ተጫራቾች ጨረታ ከተከፈተ በኃላ ተሸከርካሪዎችን ይዞ በመቅረብ በሙያተኛ የቴክኒክ ፍተሻ ይደረጋል ቴክኒክ ፍተሻ እና ፋይንሻል በመገምገም ባሉት የስራ ቀናት ውስጥ አሸናፊውን የምናሳውቅ ይሆናል። የአውቶቢስ ሰርቪስ እና የሃይሩፍ ሰርቪስ አገልግሎቶች የሚሰጡት ቦታ አዋሽ አርባ ከተማ (አፋር ክልል ከአዲስ አበባ 240 ኪ/ሜ) የሚገኘው የውጊያ ቴክኒክ ት/ቤት ይሆናል።
የውጊያ ቴክኒክ ት/ቤት እንደ አስፈላጊነቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማብራሪያና ጨረታ ሰነድ ማስገቢያ
ሀ. ተጫራቾች ሚኖራቸው ጥያቄ ፡- የውጊያ ቴክኒክ ት/ቤት ግዥ ዴስክ ስቁ 033 540 0612/ 09 24 84 62 69/
ፋክስ: 033 540 0666 አዋሽ አርባ
ለ. ጨረታ ሰነድ ማስገቢያ፡- መከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ጃንሜዳ ማጮ ግቢ ቃኞ ሻለቃ አደባባይ አጠገብ
ቢሮ ቁጥር፡ 006 ስልክ፡ +251 11 122 6507/ 09 42 89 99 27/
ሐ. ሰነዱ ወጪ የሚሆንበት አድራሻ፡- መከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ጃንሜዳ ማጮ ግቢ ቃኞ ሻለቃ አደባባይ
ስልክ፡ +251 11 122 6507/ 09 42 89 99 27 ቢሮ ቁጥር፦ 006
መ. ጨረታው የሚከፈትበት አድራሻ፦ መከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ጃንሜዳ ማጮ ገቢ ቃኞ ሻ/ቃ አጠገብ 6/ለ/ ይመልከቱ
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ የውጊያ ቴክኒክ ት/ቤት / አዋሽ አርባ
Tender details
- Deadline: 2026-07-01
- Bid closing time: 14:30
- Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-07-01 15:00
- Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: በኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር በስልጠና ዋና መምሪያ የውጊያ ቴክኒክ ት/ቤት
- Buyer address: አዋሽ አርባ ከተማ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published: Jun 22, 2026
- Posted at: 2026-06-23T08:22:23.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.