በአብክመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በሰንበቴ ከተማ አስተዳደር የሰንበቴ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ጠቅላላ ስፋቱ 615 ካሬ ሜትር የሆነ ለንግድ ለሆቴል አገልግሎት የሚውሉ የልማት ቦታን በመደበኛ ጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ማስተላለፍ ይፈልጋል

Description

የሁለተኛ ዙር የመሬት ሽያጭ
የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

በአብክመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በሰንበቴ ከተማ አስተዳደር የሰንበቴ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 ከ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት በሰንበቴ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ጠቅላላ ስፋቱ 615 ካሬ ሜትር የሆነ ለንግድ ለሆቴል አገልግሎት የሚውሉ የልማት ቦታን በመደበኛ ጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ማስተላለፍ ይፈልጋል። 

ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመሳተፍ ፍቃድኛ የሆኑ ተጫራቾች፡-

1. የጨረታውን ሰነድ በሰንበቴ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቡድን ቢሮ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ሸያጭ የማይመለስ የኢትዮ. ብር 1500.00 /አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።

2. ተጫራቾች ቦታው የሚገኙበት ድረስ በመሄድ አጠቃላይ የቦታውን ሁኔታ በማየት ዋጋ ማቅረብ ይችላሉ።

3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው ስፔስፊኬሽን / Specification | መሰረት መሆን ይኖርበታል፣

4. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ጠቅላላ ቦታ ስፋት በሊዝ መነሻ ዋጋ ተባዝቶ ከሚገኘው ውጤት 30 በመቶ ያላነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ ከፍያ ማዘዣ /CPO/ ማስያዘ ይኖርባቸዋል። ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይንም ከ 30 ከመቶ ቢያንስ ተጫራቹ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከውድድር ይሰረዛል።

5. ተጫራች የጨረታውን ሰነድ፣ ሲፒኦ እና ሌሎች የጨረታ ሰነዶችን በታሸገ ኤንቨሎፕ በአብክመ አ/ብ/ዞን በሰንበቴ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቡድን ቢሮ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን 16/10/2018 ዓ.ም እስከ 29/10/2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6. ጨረታው የሚዘጋበት ቀን 29/10/2018 ዓ.ም 11፡00 ሰዓት ይሆናል።

7. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ30/0/2018 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት በሰንበቴ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

8. በጋራ ተደራጅተው በአከሲዮን/እነ በሚል ሰነድ ለመግዛት የሚፈልጉ አካላት ከሚመለከተው አካል እነ የተባላችሁበትን ህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ መረጃ ከነ አባላት ስም ዝርዝር የድርጅቱ ማህተም አርፎበት ሰነድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

9. ቦታውን ለመጎብኘት ለሚፈልጉ ተጫራቾች ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት ለሽያጭ የተዘጋጁ ቦታዎች በሚገኙበት በሰንበቴ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በሚመድባቸው አስጎብኝዎች ቦታዎቹን መመልከት ይችላሉ።

10. የአካባቢውን ወቅታዊ የሊዝ ጨረታ መነሻ ዋጋ እና ሌሎች የከተማ መሬትን በሊዝ ለማስተዳደር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 721/2004 መሰረት በማድረግ በሰንበቴ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ መመልከት ይችላሉ።

11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልከ ቁጥሮች 09 12 87 19 93 / 09 39 69 82 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የሰንበቴ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-06
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid opening: 2026-07-07 10:00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Senbete City Administration Finance Office
  • Bid bond: 30 በመቶ ያላነሰ
  • Bid document price: 1500.00 /አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር/ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ
  • Published: Jun 23, 2026
  • Posted at: 2026-06-23T09:06:52.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders