የኢ.ፌ.ዴ.ሪ አየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ ተሽከርካሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ አየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ ለ2019 በጀት ዓመት ለሠራተኞች ሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጡ አውቶብሶች፣ ሃይሩፎችንና ዶልፊኖችን 1ኛ/ ከአዲስ አበባ ቢሾፍቱ ሐረር ሜዳ ደርሶ መልስ 2ኛ ከአዳማ ቢሾፍቱ /ሐረር ሜዳ/ ደርሶ መልስ 3ኛ/ ከዱከም ቢሾፍቱ ሐረር ሜዳ/ በቀጥታ የደርሶ መልስ አገልግሎት የሚሰጥ 4ኛ/ ቢሾፍቱ ዙሪያ ምልልስ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለፁትን መመሪያና ግዴታዎች ማሟላት አለባቸው።
- ተጫራቾች ለወጣው ጨረታ በዘርፉ የተሰማሩ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ከንግድ ሚኒስቴር የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የምዝገባ ሠርተፍኬት፣ የንብረት ባለበትነት ማረጋገጫ (ሊብሬ)፣ እንዲሁም የሶስተኛ ወገን ኢንሹራንስ የገበሩበት ዶክመንት ያላቸው ሆነው የተጠቀሱትን ሰነዶች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማቅረብና ዋናውን ቅጅ ሲጠየቁ ለኮሚቴው ማሳየት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ትክክለኛ ሙሉ አድራሻቸውን፣ ስማቸውንና ፊርማቸውን በጨረታ ሠነዱ ላይ በግልፅ ማስፈር አለባቸው። ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነድና ፋይናንሻል ሰነዱን ለየብቻ ታሽጎ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ። በተጨማሪ በፖስታው ላይ የተወዳደሩበትን የጨረታ ቁጥር ማስፈር ይጠበቅባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች በሌላ ድርጅት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይፈቀድም።
- ተጫራቾች የተሽከርካሪ አይነት፣ የመቀመጫ ወንበር ብዛት፣ በቀን የክፍያ መጠንና የሠሌዳ ቁጥር በትክክል በሠነዱ ላይ ባለው መሰረት ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሰነዱ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት 15/10/2018 ዓ.ም ጀምሮ በተከታታይ ባሉት 10 የስራና የበዓል ቀናቶችን ጨምሮ የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ቢሾፍቱ ከተማ ከሚገኘው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ አየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ ዋና በር በመምጣት ሰነዱን መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ኪሎቻቸው በተገኙበት 24/10/2018 ከቀኑ 6፡00 ተዘግቶ ከሰዓት 7፡30 ላይ ቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘው የአየር ኃይል መኮንኖች ክበብ ውስጥ ይከፈታል።
- ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሠነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ 3,000.00 /ሶስት ሺህ/ ብር በባንክ በተመሰከረለት የባንክ ቼክ / ሲፒኦ/ ማስያዝ ግዴታ አለባቸው። ይህ ሂሣብ አሸናፊው እንደተለየ ለተሸናፊው ሙሉ በሙሉ ተመላሽ የሚደረግ ሲሆን ለአሸናፊ ተጫራቾች ውል አስረው ስራ እንደጀመሩ ተመላሽ ይደረጋል።
- አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ውል እንዳሰሩ ተሽከርካሪዎቻቸው የሚውሉበት አየር ኃይል በሚያዘጋጀው ቦታ ይሆናል።
- በአንድ መኪና ከአንድ መስመር በላይ መጫረት አይቻልም።
- የጨረታው አሸናፊዎች ማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ3 ቀናት ጊዜ ውስጥ ውሉን መፈረም ይኖርባቸዋል።
- ተወዳደሪዎቹ የተሽከርካሪ ቴክኒካል ፍተሻ መስሪያ ቤቱ በሚያቀርብው ፕሮግራም መሰረት ተሽከርካሪዎቻቸውን ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃና ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0114 33 84 03 ወይም 0114 33 80 40
የውስጥ መስመር 1330/1446 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
NB ቢሾፍቱ ዙሪያ ላላቹ ተወዳዳሪዎች በቀን 100 ኪ.ሜ በመሸፈን ሥራን ለመስራት ፍቃደኛ የሆነ።
የአየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-07-01
- Bid closing time: 12:00
- Bid opening: 2026-07-01 13:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: የአየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ
- Bid bond: 3,000.00 ብር
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: Jun 22, 2026
- Posted at: 2026-06-23T09:58:31.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.