የጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ የመኪና ኪራይ ለመከራየት እና በሆስፒታሉ ግቢ ውስጥ የሚገኙ ብረታ ብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅቱ ውል ይዞ ለመከራየትና ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል

  • ለሰራተኞች ሰርቪስ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ የመኪና ኪራይ ለመከራየት እና
  •  በሆስፒታሉ ግቢ ውስጥ የሚገኙ ብረታ ብረቶችን

በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅቱ ውል ይዞ ለመከራየትና ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ 

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1.  በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2.  የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3.  ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የተሞላውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 በመቁረጥ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በ2 ፖስታ በማሽግ ዋናና ቅጅ በማለትና በማሸግ ሙሉ ስም፣ የድርጅቱን ማህተም አድራሻውን ከፖስታው ላይ በመፃፍ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራች በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመ/ቤታችን ግ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታ ከወጣበት ቀን ከሰኔ 15/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡ ጨረታው በ16ኛው ቀን ማለትም ሰኔ 30/2018 ዓ.ም 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  7.  የመኪና ኪራይና የብረት ሽያጩ አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. የጨረታ ሰነዱ ሥርዝ ድልዝ ወይም በፍሉድ የተስተካከለ ከሆነ ሰነዱ ተቀባይነት የለውም ወይም መፈረም አለበት፡፡
  9. ተጫራቾች ከዚህ በፊት በአገልግሎት አሰጣጥ ቅሬታ ያልቀረበባቸው መሆን አለባቸው፡፡
  10. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ይካሄዳል፡፡ ጨረታው ሲከፈት ያልተገኙ ተጫራቾች በዕለቱ ለሚተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
  11. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመ/ቤታችን ዋና ገ/ያዥ ማካኝነት በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  12. ክፍያ በሚፈጸምበት ወቅት በስማቸው /በድርጅቱ/ የተሰራ ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  13.  ከአማካኝ የገቢያ ጥናት ዋጋ በላይ የሞላ ተጫራች ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡
  14. ጨረታ የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 23 22 10 87 /09 18 22 05 04 /09 18 21 06 28 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል


Tender details

  • Deadline: 2026-07-07
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-07-07 10:30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Ayera General Hospital
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: Jun 22, 2026
  • Posted at: 2026-06-23T12:49:34.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders