በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የጉና በጌ ምድር ወረዳ የክምር ድንጋይ መሪ ማዘጋጃ ቤት ለመኖሪያ አገልግሎት 8 (ስምንት) ለድርጅት 1 (አንድ) ቦታዎችን ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የጉና በጌ ምድር ወረዳ የክምር ድንጋይ መሪ ማዘጋጃ ቤት የከተማ ቦታ በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 እና በሊዝ መመሪያ ቁጥር 1/2005 መሰረት 2018 በጀት ዓመት 1.ኛ ዙር በጨረታ ለመኖሪያ አገልግሎት 8 (ስምንት) ለድርጅት 1 (አንድ) ቦታዎችን ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
1. መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) የሥራ ቀናት ከ2፡30 እስከ 11፡ 30 የማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ ብር) በመክፈል ቢሮ ቁጥር 6 መግዛት ይችላሉ፡፡
2. ጨረታው የሚዘጋው በ10 ኛው ቀን በ11፡30 ይሆናል፡፡
3. ጨረታው የሚከፈተው ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በ3፡00 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በክምር ድንጋይ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት አዳራሽ ይሆናል፡፡
4. መስሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
5. ቦታውን ለመጎብኘት ከፈለጉ ከጨረታ ኮሚቴ ጋር መጎብኘት ይችላሉ፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ሲፒኦ) ለድርጅት 15 በመቶ እንዲሁም ለመኖሪያ 10 በመቶ ህጋዊ ከሆነ ባንክ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
7. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ በጽ/ቤቱ የውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳ ወይም በስልክ ቁጥር 09 18 71 44 11 ደውለው መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የክምር ድንጋይ መሪ ማዘጋጃ ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-07-02
- Bid closing time: 17:30
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ኛው ቀን በ11፡30
- Bid opening: 2026-07-03 12:00
- Bid opening (note): ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በ3፡00
- Region: Amhara
- Publishing entity: Kimer Dingay Municipality
- Bid bond: ለድርጅት 15 በመቶ እንዲሁም ለመኖሪያ 10 በመቶ
- Bid document price: 400 (አራት መቶ ብር)
- Published: Jun 22, 2026
- Posted at: 2026-06-23T13:22:10.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.