የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር መሬት መምሪያ ለመኖሪያ እና ንግድ አገልግሎት የተዘጋጁ ቦታዎችን በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል
Description
የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር መሬት መምሪያ የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 በፊደል ተራ ከ”ሀ” እስከ “ሠ” በተዘረዘረው መሰረት ለመኖሪያ እና ንግድ አገልግሎት የተዘጋጁ ቦታዎችን በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
1. የጨረታ ቁጥር፡ ደማ/02/2018
2. የጨረታ ዙር፡ 2ኛ
3. የጨረታው ዓይነት፡- መደበኛ
4. መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ከአገልግሎት አቅርቦት ተጠሪ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በስራ ሰዓት መግዛት ይችላል፡፡
5. ጨረታው በ10ኛው ቀን ሰነድ የሚሸጠው እስከ ቀኑ 10፡00 ብቻ ይሆናል፡፡
6. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡00 ብቻ ይሆናል፡፡
7. የጫረታው ሳጥን የሚታሸገው ይህ ማስታወቂያ በበኩር ጋዜጣ በወጣበት በ10ኛው ቀን ከቀኙ 11፡00 ሰዓት ብቻ ነው
8. ቦታውን መጎብኘት ለሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጉብኝት ፕሮግራም በውስጥ ማስታወቂያ የምናሳውቅ ይሆናል፡፡
9. ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 በመምሪያው ግቢ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡
10. ጨረታው 11ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
11. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ የተጫረቱበትን የቦታ ስፋት በቦታው የመነሻ ዋጋ በማባዛት የሚገኘውን ዉጤት ከ20 በመቶ ያላነሰ በዝግ አካውንት በማስገባት በባንክ የተመሰከረለት ሰነድ ከዋጋ እና የሃሳብ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
12. በጨረታው ለተሸነፉ ተወዳዳሪዎች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተመላሽ የሚደረገው የጨረታው አሸናፊ ከተረጋገጠበት ከሚቀጥለው ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ይሆናል፡፡
13. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
14. ስለጨረታው ዝርዝር ማብራሪያ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር መሬት መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-07-02
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): በ10ኛው ቀን ከቀኙ 11፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-07-03 12:00
- Bid opening (note): በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00
- Region: Amhara
- Publishing entity: የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር መሬት መምሪያ
- Bid bond: ከ20 በመቶ ያላነሰ
- Bid document price: 500 (አምስት መቶ ብር)
- Published: Jun 22, 2026
- Posted at: 2026-06-23T13:27:26.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.