አማራ ባንክ አ.ማ. የተለያዩ ንብረቶችን መሸጥ ይፈልጋል

Description

የሐራጅ ማስታወቂያ ቁጥር አማራ ባንክ 42/2018

አማራ ባንክ አ.ማ. በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ከዚህ ቀጥሎ የቀረበውን ንብረት በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል 

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ

ተቁ

የተበዳሪው ስም

 

የንብረት አስያዥ ስም

 

አበዳሪው ቅርንጫፍ

 

የንብረቱ አድራሻ

የቦታው ስፋት

 

የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ ቁጥር

 

የንብረቱ ዓይነት/ የይዞታው አገልገሎት

የጨረታ ነሻ ዋጋ /ብር/

 

ጨረታው የሚከናወንበት

/ከተማ

ከተማ

ወረዳ

ቀበሌ

ቀን

ሰዓት

ቦታ

1

ሲሳይ አስንቆ ከበደ

 

ሲሳይ አስንቆ ከበደ

ቦሌ ፍላሚንጎ

 

አቃቂ ቃሊቲ

 

አዲስ አበባ

 

04

-

75.59 ካሬ ሜትር 

AA0000704057141670323

 

መኖሪያ (ኮንዶሚንየም)

 

4,052,295.39

 

ሐምሌ 21 ቀን 2018 .

3:00 እስከ 400 ሰዓት

 

አማራ ባንክ አ.ማ. ዋና መሥሪያ ቤት 18 ወለል

2

ፀጋዬ ገላና / ማርያም

 

ፀጋዬ ገላና / ማርያም

ወሊሶ

 

-

ወሊሶ

 

-

02

200 ካሬ ሜትር

W/4155/99

 

መኖሪያ

2,883,054.26

 

ሐምሌ 21 ቀን 2018 .

4:00 እስከ 500 ሰዓት

አማራ ባንክ አ.ማ. ዋና መሥሪያ ቤት 18 ወለል

3

መስፍን መንግሥቱ ውድነህ

 

መስፍን መንግሥቱ ውድነህ

 

ባህርዳር

 

ግንቦት 20

 

ባህርዳር

 

-

14

3000 ካሬ ሜትር

32541/2010

 

ለኢንዱስትሪ

 

41,996,341.54

 

ሐምሌ 21 ቀን 2018 .

3:00 እስከ 400 ሰዓት

አማራ ባንክ አ.ማ. ባህር ዳር ዲስትሪክት ቢሮ

 

እታገኘሁ ሁነኛው

ባህርዳር

 

ጣና

ባህርዳር

 

-

16

244 ካሬ ሜትር

16411/98

 

መኖሪያ

7,745,444.22

 

ሐምሌ 21 ቀን 2018 .

4:00 እስከ 500 ሰዓት

 

አማራ ባንክ አ.ማ. ባህር ዳር ዲስትሪክት ቢሮ

4

ምድረ ፈውስ የጥራጥሬ እህሎች ላኪነት /የተየግማህበር

/ መላኩ የኔነህ ፈንታ

 

ፍኖተ ሰላም

 

-

ፍኖተ ሰላም

 

-

02

622 ካሬ ሜትር

4632/2009

 

ለድርጅት

45,412,901.88

ሐምሌ 21 ቀን 2018 .

5:00 እስከ 600 ሰዓት

አማራ ባንክ አ.ማ. ባህር ዳር ዲስትሪክት ቢሮ

5

ጥሩ ኤ እርሻ /የተየግማህበር

ካሳሁን እውነቴ አለልኝ

 

በላይ ዘለቀ

 

ጣና

ባህርዳር

 

-

-

6000 ካሬ ሜትር

ባህኢፓ/0062/09

ለኢንዱስትሪ

 

62,133,310.57

 

ሐምሌ 21 ቀን 2018 .

7:00 እስከ 800 ሰዓት

 

አማራ ባንክ አ.ማ. ባህር ዳር ዲስትሪክት ቢሮ

ማሳሰቢያ፡-

1.ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4 ወይም ሃያ አምስት በመቶ (25%) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ (CPO) ብቻ በአማራ ባንክ አማ ስም በማሠራት በማስያዝ እና በመመዝገብ በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ።

2. ከፍተኛ ዋጋ የሰጠው ተጫራች የጨረታው አሸናፊ ነው የሚባለው ከባንኩ አሸናፊነቱን የሚገልጽ ደብዳቤ በጽሑፍ ሲደርሰው ብቻ ነው።

3. የጨረታ አሸናፊው አሸናፊ መሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ አጠናቆ መከፈል ይኖርበታል፡፡ ባይከፍል ግን የሐራጁ ውጤት ተሰርዞ ያስያዘው ሲፒኦ አይመለስለትም፤ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡ ላላሸነፉት ተጫራቾች ግን ያስያዙት ሲፒኦ በዕለቱ ይመለስላቸዋል።

4. የሐራጁ አሸናፊ ገዥ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግሥት የሚከፈሉ ክፍያዎችን የሊዝን ክፍያን ጨምሮ፤ ግብር፤ በዋጋው ላይ የሚታሰብ ተጨማሪ እሴት ታክስ (15%) ካለ ከስም ማዘዋወሪያ ጋር የተገናኙ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ታክስ እና ግብሮች ገዥው አሸናፊው/ ይከፍላል።

5. ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ (የቀበሌ፤ የመንጃ ፍቃድ፤ ፓስፖርት ወይም ብሄራዊ መታወቂያ) መያዝ ይገባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የሕግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ደግሞ ሕጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስከር ወረቀት እና ሐራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ግለሰብ ሥልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት የጸደቀ መመስረቻ ጽሑፍ (የመተዳደሪያ ደንብ)፤ ቃለጉባኤ ወይም የውከልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት።

6. ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚለከተው መንግሥታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል።

7. ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጉብኝት ፕሮግራም ከወርካውትና ሪከቨሪ ክፍል ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ ጨረታው ከመካሄዱ ከ5 ቀን በፊት መጎብኘት ይችላል።

8. ጨረታው በሰንጠረዡ ላይ በተጠቀሰው ቀን፤ ሰዓትና ቦታ ተጫራቾች፤ ተበዳሪ እና ንብረት አስያዥ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ይካሄዳል፡፡ ነገር ግን ተበዳሪውም ሆነ መያዣ ሰጪው ባይገኙ ጨረታው በሌሉበት ይካሄዳል።

9. ንብረቱን/ቶቹን በጨረታ አሸንፎ የገዛ ግለሰብ ድርጅት የሽያጭ ገንዘቡን ከፍሎ ባጠናቀቀ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን መረከብ ያለበት ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ንብረቱን ካልተረከበ በንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ባንኩ ኃላፊነቱን አይወስድም፡፡ ገዥው በተጠቀሰው ጊዜ ንብረቶቹን ካልተረከበ ከንብረቶቹ ጋር በተያያዘ ለሚኖር ወጪ ኃላፊነቱን ይወስዳል።

10 በባንኩ የብድር ፖሊሲ መመሪያ እና ቅድመ ሁኔታ መሰረት የሚፈለገውን ማስረጃ አሟልቶ ለቀረበ የጨረታ አሸናፊ ባንኩ ብድር ሊያመቻች ይችላል።

11. የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት 30 ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል።

12. በወንድ አንቀጽ የተጠቀሰው ለሴት እና ሕጋዊ ሰውነት ላላቸው ድርጅትም ያገለግላል።

13. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

14. ለበለጠ ማብራሪያ አማራ ባንከ አ.ማ. 011 558 2764 ወይም 011 558 4189 በሥራ ሰአት ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

አማራ ባንከ አ.ማ.


Tender details

  • Deadline: 2026-07-28
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): የጨረታ መዝጊያ ሰአት የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-07-28 14:00
  • Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ሰአት የተለያየ ነው
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Amhara Bank S.C.
  • Bid bond: 25%
  • Published: Jun 24, 2026
  • Posted at: 2026-06-24T07:56:06.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders