አቢሲንያ ባንክ አ.ማ. የቦታው ስፋት በካ.ሜ. 469 ካ.ሜ የሆነ መኖሪያ ቤት ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውን እና በሠንጠረዡ የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ንብረቱ ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፣ በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

  • ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋውን 1/4 (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው ለመሳተፍ ይችላሉ።
  • የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል። በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል። በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል።
  • ተበዳሪው /መያዣ ሰጪው/ በሐራጁ ቀን እና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ። ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።
  • የጨረታው አሸናፊ ከሚገዙት ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ የሊዝ ክፍያ፣ ግብር እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎችን ገዢ ይከፍላሉ።
  •  በባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መሰፍርቱን ለሚያሟሉ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢዎች ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል።
  •  ንብረቱን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ ለመጎብኘት ወይም ለማየት ይቻላል።
  •  ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 047-211-3304 / 047-211-3312/ ጅማ ዲስትሪክት በመደወል መጠየቅ ይቻላል። 
  •  ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በማናቸውም ጊዜ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

..

የተበዳሪው ስም

 

የመያዣ ስጪው ሰም

 

ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ

 

የጨረታው መነሻ ዋጋ በብር

ጨረታው የሚካሄድበት ቀንና ዓ.ም.

የምዝገባ ሰዓት

 

የጨረታው ሰዓት

ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ

የንብረቱ አይነትና አገልግሎት

የቦታው ስፋት በካ.ሜ.

 

የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር

የጨረታው ማስታወቂያ የወጣበት ጊዜ

1

አቶ ነጋሲ አለማየሁ

 

ተበዳሪው

 

ጋምቤላ ከተማ፤ ቀበሌ 05

 

6,814,313.52

 

ሐምሌ 23 ቀን 2018 .

 

4:00 -5:00

 

5:00 -5:30

 

አቢሲንያ ባንክ ባሮ ማዶ ቅርንጫፍ

 

መኖሪያ ቤት

 

469 .

 

34670/04

 

ለሶስተኛ

 

 


Tender details

  • Deadline: 2026-07-30
  • Bid closing time: 11:30
  • Bid opening: 2026-07-30 11:30
  • Region: Gambela
  • Publishing entity: Bank of Abyssinia S.C.
  • Buyer address: Addis Ababa Ethiopia
  • Bid bond: 25%
  • Published: Jun 24, 2026
  • Posted at: 2026-06-24T08:43:56.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders