የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የሰራተኛ መዝናኛ ክበብ አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉ ድርጅቶች ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር አ/ቃ/ፐ/006/2018
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የሰራተኛ መዝናኛ ክበብ አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉ ድርጅቶች ማወዳደሪያ መስፈርቶች
1. የህጋዊነት ጉዳዮች በተመለከተ ዕጩ ተወዳደሪዎች በዘርፉ ማለትም በሬስቱራንት ወይም በሆቴል አገልግሎት ዘርፉ የግብር ከፋይነት ምዝገባ እንዲሁም የተ.እ.ታ (ቫት) ተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈለ የንግድ ምዝገባና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ምስክር ወረቀት ከጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ ከላይ የተሰጡትን መስፈርቶች ማሟላት እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪ ካደራጃቸው የመንግስት ተቋም 6 ወር ያላለፈ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
2. የስራ ልምድ በሬስቱራንት ፣በባርና ሬስቱራንት ወይም በሆቴል አገልግሎት እንዲሁም ለጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተቋማት የስራ አገልግሎት ዘርፍ ከ1 ዓመት በላይ የስራ ልምድ ያለውና አሁንም በዘርፉ አገልግሎት እየሰጠ ያለ ስለመሆኑ መረጃ ማቅረብ የሚችል
3. የሰው ሀይል ድርጅቱ ቢያንስ 2000 ተጠቃሚዎችን ማስተናገድ የሚችል የሆቴል መስተንግዶ የሰው ሀይል መዋቅር አደረጃጀት ያለውና ማናጀር፣ ሼፎች ምግብ አዘጋጆች፣ አስተናጋጆች ወዘተ መዋቅር ያለውና በድምሩ ቢያንስ 13 ሰራተኛ ያለው
4. የተሽከርካሪ ሁኔታ ድርጅቱ አገልግሎቱን በተገቢው ሁኔታ ማከናወን እንዲችል የሚያስችሉት ተሽከርካሪዎች ያለው ለምሳሌ ግብዓት ሊያቀርቡ የሚችሉ የጭነት ተሽከርካሪ ወዘተ ያለው
5. ተፈላጊ የጨረታ ማስከበሪያ CPO ብር 40,000.00 (አርባ ሺህ ብር) ሲሆን (CPO ሲያሰሩ ለአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ብለው ያሰሩ)
6. በድርጅቱ የሚሸፈኑ ግብዓቶችን በተመለከተ ድርጅቱ የውሃ፣ የመብራት እንዲሁም የቤት ኪራይ የማያስከፍል መሆኑ እና ድርጅቱ የራሱ እቃዎች ያሉት መሆኑ እና አሸናፊው አካል የራሱን ተጨማሪ እቃ በማስመዝገብ አስገብቶ መስራት የሚችል መሆኑ
7. የተጠየቀውን የጨረታ ማስከበሪያ እንዲሁም ቢያሸንፉ የውል ማስከበሪያ CPO / የባንክ ዋስትና /በጽ/ቤታችን ስም አሰርቶ ማቅረብ የሚችል
8. ለመንግስት ንብረት ጥንቃቄ በማድረግ በሚሰራና በራሱ ወይም በሰራተኞቹ ጥንቃቄ ጉድለት ምክንያት በመገልገያ ቁሳቁስና ህንጻ ላይ ብልሽት ቢደርስ ወይም ጥፋት ቢከሰት መልሶ ለመተካት አልያም ካሳ ለመክፈል ፍቃደኛ መሆኑን ማረጋገጫ ደብዳቤ በድርጅቱ ፈርማ እና ማህተም ማረጋገጥና ማቅረብ የሚችል።
9. ለካፌ ለሆቴል መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ ዝርዝር የያዘውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ የሚችሉ ሲሆን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በፐ/ሰ/የሰ/ሀ/ ል/ፅ/ቤት የግዥ አስተዳደር ቡድን 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 508 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
10. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ መሙላት ያለባቸው ቫትን ጨምሮ ያለውን ዋጋ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ ኦርጅናል ላይ ኦርጅናል ኮፒ ላይ ኮፒ በማለት በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር (10) ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ አየር ላይ በማዋል በአስራ አንደኛው የስራ ቀን እስከ 4፡00 ሰዓት ብቻ ተጫራቾች ሰነድ በማስገባት 4፡00 ሰዓት ላይ ጨረታው ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 508 ጨረታው ይከፈታል።
11. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ የድርጅታቸውን አድራሻ ስም፣ ማህተምና ፊርማ ማስፈር ይኖርባቸዋል።
12. ተጫራቾች ላሸነፉት ግብዓት የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 30% ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
13. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፡- አድራሻ፡- ከቃሊቲ መናኽሪያ ፊት ለፊት ባለው የአስተዳደሩ ህንፃ ላይ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 508 መጠየቅ ይቻላል።
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-07-08
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር (10) ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ አየር ላይ በማዋል በአስራ አንደኛው የስራ ቀን እስከ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-07-08 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር (10) ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ አየር ላይ በማዋል በአስራ አንደኛው የስራ ቀን እስከ 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Akaki Kaliti Sub City Public Service and Human Resource Development Office
- Buyer address: ከቃሊቲ መናኽሪያ ፊት ለፊት ባለው የአስተዳደሩ ህንፃ ላይ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 508
- Bid bond: 40,000.00 (አርባ ሺህ ብር)
- Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
- Published: Jun 26, 2026
- Posted at: 2026-06-26T08:15:26.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.