የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት እነ አቶ አጥናፍ ታቼ እና በፍ/ባለዕዳ ወ/ሮ እመቤት መንክር መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ/56277 28/03/2010 ዓ.ም እና በመ/ቁ 102847 በ23/3/2015 ዓ.ም በመ/ቁ 103388 በ15/2/2015 ዓ.ም በመ/ቁ 104308 በ01/06/2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 02 የቤት ቁጥር 214 ካርታ ቁጥር አከ-05/18/1/5444/ አካርታ በእነ እማማ ጨርቆስ ስም የተመዘገበ አዋሳኞቹ በምዕራብ መንገድ በሰሜን በጂ.አይ.ኤስ መረጃ ላይ ፓርሴል የውስጥ ቤት ቁጥር 210፣ 211፣ 212፣ የተገለጹ ቤቶች በምስራቅ በጂ.አይ.ኤስ መረጃ ላይ ፓርሴል 3 ውስጥ በቤት ቁጥር 189፣ 191፣ 192 የተገለጹ ቤቶች እንዲሁም በጂ.አይ.ኤስ መረጃ ላይ ፓርሴል 4 ውስጥ በቤት ቁጥር 193፣ 194፣ 195 በደቡብ በጂ.አይ.ኤስ መረጃ ላይ ፓርሴል 11 ውስጥ በቤት ቁጥር 215፤ 216፣ 217፣ 218፤ 219፣ 220፣ 195 የተገለጹ ቤቶች የሚያዋስኑት ሆኖ የቦታ ስፋት 216.61 ካ/ሜ ቦታው ከጠቅላላው ይዞታ 23.27 ካ/ሜ መንገድ የሚነካው ሆኖ የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 14,658,429.09 (አስራ አራት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሃምሳ ስምንት ሺህ አራት መቶ ሃያ ዘጠኝ ከ09/100) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ የተያዘ ቢሆንም በዕለቱ ምንም ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል። ስለሆነም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.102847 በ05/10/2018ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ድጋሚ ሐራጅ ሆኖ 1/4ኛ 3,664,607.27 (ሶስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ስልሳ አራት ሺህ ስድስት መቶ ሰባት ከ27/100) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው, ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። 1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚያመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፤ በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ, ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 11 273 0852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-07-27
- Bid closing time: 11:00
- Bid opening: 2026-07-27 11:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published: Jun 27, 2026
- Posted at: 2026-06-27T07:08:36.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.