በየካ ክ/ከ የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ ጤና ጣቢያ የካፌ አገልግሎት እና በየወሩ ለሚደረገው ሚኒሰትሪሚንግ ፕሮግራም መስተንግዶ የምግብና መጠጥ አቅርቦት በአገር አቀፍ ብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መስጠት ይፈልጋል
Description
ብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨ.መ.ቁ. KVMHC-03/18
በየካ ክ/ከ የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ ጤና ጣቢያ የካፌ አገልግሎት እና በየወሩ ለሚደረገው ሚኒሰትሪሚንግ ፕሮግራም መስተንግዶ የምግብና መጠጥ አቅርቦት ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን በአገር አቀፍ ብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መስጠት ይፈልጋል።
- ሎት 1 የካፌ አገልግሎት
- ሎት-2. ለሚኒሰትሪሚንግ ፕሮግራም የምግብና መጠጥ አቅርቦት
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች፡-
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የቲን(TIN) እና የቫት(VAT) ተመዝጋቢ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ/ ብር ብቻ በመክፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከተቋሙ ረዳት ፋይናንስ ክፍል 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 303 በመውሰድ እና የጨረታ ሰነዱ ላይ የሚጫረቱበትን ዋጋ ከነቫት በመሙላት እና ስም፣ ፈርማና የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፕ በመ/ቤቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ/CPO/
|
ሎት |
1 |
2 |
|
ብር |
3,000.00 |
2,000.00 |
4, ጨረታው የሚከፈተው ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነድ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን በዚሁ ቀን 3፡30 ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በይፋ ይከፈታል።
5. ካፌውን በአካል ማየት የሚቻል መሆኑን እና ካፌው ምንም ዓይነት እቃ የሌለው በመሆኑ ይህን መሟላት የሚችል።
6. መ/ቤቱ በስራ ቀን 40/አርባ /ብር በወር እስከ 880/ስምንት መቶ ሰማኒያ/ ብር ኩፖን ለአንድ ሰራተኛ ይደጉማል።
7. ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡- ሚኒሊክ ሆስፒታል የካ ክ/ከ ወረዳ 4 አስተዳደር ጽ/ቤት ጎን;
ለበለጠ መረጃ ስ.ቁ 011 122 0624/0350
በየካ ክ/ከተማ ጤ/ጽ/ቤት የኮሪያ ዘማቾች
መታሰቢያ ጤና ጣቢያ
Tender details
- Deadline: 2026-07-09
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-07-09 12:00
- Bid opening (note): ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Korea War Veterans Memorial Health Post
- Buyer address: ዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል ጀርባ በሬሳ መውጫ በኩል ገባ ብሎ ከየካ ወረዳ-4 አስ/ጽ/ቤት አጠገብ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 100 (አንድ መቶ ብር)
- Published: Jun 27, 2026
- Posted at: 2026-06-27T07:17:21.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.