Catering and Cafeteria Services
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ግብርና ቢሮ የወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ በ2018 ትምህርት ዘመን የሪፍሬሽመንት አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ወጪውም የ2019 በጀት ዓመት አካል እንዲሆን ይፈልጋል
Description
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 008/ 2018
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ግብርና ቢሮ የወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ በ2018 ትምህርት ዘመን ለሶስት ተከታታይ ዓመታት ያስተማራቸውን ተማሪዎችን በቀን 11/11/2018 ዓ/ም ለሚያስመርቀው የምረቃ ፕሮግራም በዕለቱ ለታዳሚዎች በሚቀረበው የኮሌጁ ዓመታዊ ሥራ አፈጻጸም የግንዛቤ ማስጨበጫ እና ለተመራቂ ተማሪዎች የሥራ መመሪያ የሚሰጡ ክቡር እንግዶችና ለኮሌጁ መምህራንና አስ/ር ሠራተኞች የሚሆን የሪፍሬሽመንት አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ መስፈርቱን የሚያሟሉትን አወዳድሮ ለመግዛትና ወጪውም የ2019 በጀት ዓመት አካል እንድሆን ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚችሉ ድርጅቶች።
1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን የግብር ግዴታቸውን የተወጡ፣ የተ.እ.ታ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የቲን ሰርተፍኬት /የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ በመስተንግዶ ሥራ የመልካም ስራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችል።
2. የሪፍሬሽመንት አገልግሎት ጊዜ በምረቃው ዕለት በኮሌጅ ግቢ ውስጥ በበቂ ሁኔታ ድንኳን ተክሎ የሚያቀርብ ይሆናል።
3. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጅምሮ ዘውትር በሥራ ሰዓት ለጨረታ ዶክመንቱ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በሶዶ ግብርና ኮሌጅ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተከፍቶ በሚገኘው አካውንት ቁጥር 1000018208443 በማስገባት አድቫይስ በመያዝ ወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ ግ/ክ/ን/አስ/ር ቡድን ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
4. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት ሲፐኦ ብር 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ/ ከጨረታው ሰነድ ኦርጅናል ጋር አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን ሰነድ አንድ ኦርጅናልና 1 የኦርጅናሉን ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በስም በታሸገ ኤምቨሎፕ ሙሉ አድርሻቸውን በመጥቅስ ለዚሁ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
6. የጨረታው ሳጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ15 ተከታታይ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው 16ኛ የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾችና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ሰዓት ላይ ወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ ግ/ክ/ን/አስ/ር ቡድን ቢሮ ይከፈታል። 16ኛው የሥራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ በሚውለው የሥራ ቀን ይከፈታል።
7. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ ላይ የማይነበብና ሰርዝ ድልዝ ያለው መሆን የለበትም።
8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0465513984/0916834217/ መደወል ይቻላል።
ወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ
Tender details
- Deadline: 2026-07-13
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ15 ተከታታይ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው 16ኛ የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-07-13 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ15 ተከታታይ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው 16ኛ የሥራ ቀን 4፡30 ሰዓት
- Region: South Ethiopia Regional State
- Publishing entity: Wolaita Sodo Agricultural College
- Bid bond: 30,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Jun 27, 2026)
- Posted at: 2026-06-27T07:18:03.000Z