አቢሲንያ ባንክ አ.ማ. ለኢንዱስትሪ አገልግሎት የሚዉል መጋዘን ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

አቢሲንያ ባንክ አ.ማ. ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘዉን በሠንጠረዡ የተመለከተዉን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ንብረቱ ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

  • ተጫራቾች ለጨረታ የቀረበዉን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4 (አንድ አራተኛ ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ በአቢሲንያ ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
  • የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሉ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል። በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ ያስያዘው  ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል። በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ወዲያዉ ይመለስላቸዋል።
  • ተበዳሪው/ መያዣ ሰጪው/ በሐራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ። ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።
  • የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ 15%  የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል። ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ለቀሪው የሊዝ ክፍያ ነው ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል።
  • ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ወይም ማየት ይቻላል።
  • በባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟላ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ /አሸናፊ ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል።
  • የጨረታው ቦታ አዲስ አበባ ከተማ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ለገሀር በሚገኘው የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ነው።
  • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 515 1153 እና 011 515 0711 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
  • ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተ.ቁ

የተበዳሪው ስም

የመያዣ ሰጪው ስም

የንብረቱ አይነት እና ገልግሎት

የቦታው ስፋት በካ.

የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር

ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ

የጨረታው መነሻ ዋጋ በብር

ጨረታው የሚካሄድበት ቀን

የምዝገሰዓት

የጨረታ ሰዓት

 

1

ፍራንኩን  ኢት አዉቶሞቲቭ ኢንጂነሪንግ /የተ/የግ/ማህበር

አቶ ሎኔ  ፍራንቼስኮ

ለኢንዱስትሪ አገልግሎት የሚዉል መጋዘን

በይዞታ ማረጋገጫ (ካርታ) ላይ 2500 ሲሆን፣ በመንገድ ማስፋት ምክንያት ግን ይዞታዉ ወደ 1700 ካ.ሜ ዝቅ ብሏል።

ቡ/ል/ቀ/A79-30/83

 

ገር ከተማ ቡራዩ / ከተማ

 

31,513,245.63

 

ሐምሌ 22 ቀን 2018 .

 

4:30-5:30

 

5:30-6:00

 

በድጋሚ

 

 


Tender details

  • Deadline: 2026-07-29
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid opening: 2026-07-29 12:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Bank of Abyssinia S.C.
  • Buyer address: Addis Ababa Ethiopia
  • Bid bond: 25%
  • Published: Jun 28, 2026
  • Posted at: 2026-06-29T10:06:20.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders