አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውንና በሠንጠረዡ ውስጥ የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) ለባንኮች በተሰጠው ስልጣን መሠረት ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4 (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው ለመሳተፍ ይችላሉ።
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል። በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።
- በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል።
- ተበዳሪው /መያዣ ሰጪው/ በሐራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ። ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።
- የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፤ ግብር፣ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል። ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ለቀሪው የሊዝ ክፍያ ገዢው ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል።
- ንብረቱን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ ለመጎብኘት ወይም ለማየት ይቻላል።
- በባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟላ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ /አሽናፊ ባንኩ ከፊል ብድር ሊስጥ ይችላል።
- የጨረታው ቦታ አዲስ አበባ ከተማ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 7፣ ለገሀር በሚገኘው የአቢሲንያ ባንክ አማ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ B 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የፎርክሎዠር እና ዴት ሊቲጌሽን ዲቪዥን የጨረታ ክፍል ውስጥ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 515 0711 እና 011 554 6737 አ.አ በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
|
ተ.ቁ |
የበዳሪው ስም |
የመያዣሰጪው ስም |
የንብረቱ አይነት እና አገልግሎት |
የቦታው ስፋት በካ.ሜ |
የይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር |
ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ |
የጨረታው መነሻ ዋጋ በብር |
ጨረታው የሚካሄድበት ቀን |
የመዝገባ ሰዓት |
የጨረታ ሰዓት |
|
1 |
አቶ ከድር ኡመር እንግዳ እና ኬቢ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/የማህበር |
ኬቢ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር |
B+G+3 የሆነ የንግድ (Mall) |
8555 |
33872 |
በአማ/ብ/ክ/መ ባህርዳር ከተማ ፋሲሎ ክ/ከተማ፤ ቀበሌ 15 |
178,092,297.21 |
ሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ.ም. |
4፡30-5:30
|
5:30-6፡00
|
|
2 |
ኤኤምሲ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር |
የንግድ ቤት
|
243 |
17549/98 |
በአማ ብ/ክ/መ፣ ባህርዳር ከተማ፣ ግሽ አባይ ክ/ከተማ ቀበሌ 06 |
30,062,749.76
|
ሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ.ም. |
8:30-9:30
|
9:30- 10:00 |
|
|
3 |
አቶ ከድር ኡመር እንግዳ
|
መኖሪያ ቤት
|
250 |
04/001/2490 ልዩ መለያ ቁጥር Am001050704004 |
በአማ ብ/ክ/መ፣ ባህርዳር ከተማ፣ ዳግማዊ ሚኒልክ ክ/ከተማ |
8,921,044.26
|
ሐምሌ 24 ቀን 2018 ዓ.ም. |
4፡30-5:30
|
5:30-6፡00
|
Tender details
- Deadline: 2026-07-31
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): የሐራጁ መዝጊያ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-07-31 12:00
- Bid opening (note): የሐራጁ መክፈቻ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Bank of Abyssinia S.C.
- Buyer address: Addis Ababa Ethiopia
- Bid bond: 25%
- Published: Jun 28, 2026
- Posted at: 2026-06-30T06:26:46.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.